“ልጅቷን አምጡ” የ “ጉማ አዋርድ” አዘጋጅ ዮናስ ብርሃነ ትናንት ምሽት በስካይ ላይት ሆቴል ከተካሄደው የሽልማት ስነ ስርአት በኋላ ለእስር ተዳርጓል።

June 10, 2023

በስፍራው ከነበሩ ሰዎች በደረሰኝ መረጃ መሰረት ዮናስን ሲቪል የለበሱ ደህንነቶች ከምሽቱ 5 ሰአት ገደማ ከነባለቤቱ አስረው ወስደዋቸዋል። ባለቤቱ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ብትፈታም ዮናስ አንበሳ ጋራዥ አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኝ ታውቋል።
በትናንትናው ፕሮግራም ላይ “ልጅ ማኛ” በሚል የምትታወቀው ቲክቶከር ባደረገችው ሜካፕ ምክንያት “ልጅቷን አምጡ” በሚል አዘጋጆቹ ተጠይቀው እንደነበር እና እስሩም ከእሱ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል በስፍራው የነበሩ ግለሰቦች እና ሌሎች ምንጮች አረጋግጠውልኛል።
የኔ ጥያቄ:
– ሜካፕ ተቀብቶም ይሁን ፒካፕ ተኮናትሮ ሀሳብን ሰላማዊ በሆነ መንገድ መግለፅ በቃ ተከልክሏል?
– የፕሮግራሙ አዘጋጅ የተለያየ ልብስ ለብሶ እና ሜካፕ ተቀብቶ ለሚመጣው የሀገር ህዝብ ሁሉ ሀላፊነት አለበት?
ጋዜጠኛ ኤሊያስ መሰረት እንደፃፈው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

 ዐማራ  ሕዝብ  ድርጅት (ዐሕድ) ጋዜጣዊ መግለጫዎች

Next Story

አቶ ግርማ ዋቄ ከሃላፊነታቸው ተነሱ፥ ጄ/ል ይልማ መርዳሳ ተተኩ። ”አየር መንገዱ ኢትዮጵያን አይመስልም” ጠሚ/ር አብይ አህመድ

Go toTop