እንኳን ደስ ያለሽ! (ለጋዜጠኛ መዐዛ መሐመድ)

March 7, 2023

መዐዛ ሽታ ነው፤
መልካም ውሁድ ጠረን፣
በመላ አካል ሠርጾ፣
ሕዋሳት ቀስቅሶ፣
በፍጡራን ስሜት፣
እሚሞላ ሐሴት፤

አንቺም መዐዛ ነሽ፤
በሰዎች ልቦች ውስጥ – ተስፋን እምትዘሪ፣
የሕይወትን ትርጉም እምታስተምሪ፤
ያፈራሽው ፍሬ አብቦ ጎምርቶ፣
ለትውልድ ይተርፋል፣ ተራብቶ፣ ተባዝቶ፤
በዚህች ከንቱ ዓለም እርካታ እሚገኘው፣
ራስን በድሎም ለሌሎች ሲቆም ነው።
አንቺ ተወጣሽው፣ ቤትሽንም ዘግተሽ፣
የትውልዱን ዕዳ በጀግንነት ከፍለሽ!
የከወንሽው ተግባር ማዕረግ አግኝቶ፣
የምስኪን ዜጎች ድምጽ ከሩቁ ተሰምቶ፣
ባለም ላይ አብበሽ፣ በርተሽ ስለታየሽ፣
እንኳንም ደስ ያለሽ!!

ጌታቸው አበራ
የካቲት 2015 ዓ/ም
(ማርች 2023)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ኮሚዩኒኬሽን ወይስ ፎልሲፊኬሽን? – ከመርሐጽድቅ መኮንን አባይነህ

Next Story

አለም አቀፍ የሴቶች ቀን) #March8 በሙያቸው የመጀመሪያ በመሆን በግንባር ቀደምትነት የተመዘገቡ ሴት ኢትጵያውያን

Go toTop