በሰው ና በዜጋ ላይ የተመሠረተ የመንግሥት ሥርዓት ፤ ዛሬ ና አሁን  እጅግ እንደሚያሥፈልገን የተገነዘብን ይመሥለኛል ።

December 23, 2022

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ወያኔ ፤ ( ትህነግ ፣ ህውሃት ፤… ወዘተ ። ይባል ። የሰው ሥብሥብ ነው ። ሆኖም በዘር ላይ የተመሠረተ ጠባብ የፖለቲካ ቡድን እንደሆነም ይታወቃል ። ) ከኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ጋር ታረቀ ። ” ትጥቄን እፈታለሁ ። የጦር መሣሪያም አሥረክባለሁ ። አዲስ ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም ና ነፃ ምርጫ በትግራይ እንዲካሄድ እንቅፋት አልሆንም ። ሠላምን በትግራይ ክልል ለማንገሥ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር  ተባብሬ እሰራለሁ  ። ” አለ ። ወዘተ ።   ብሎ በደቡብ አፍሪካ በፕሪቶሪያ ከተማ የሠላም ሥምምነት ሰነድ ፈረመ ። ሲባል ፣ ” እፎይ ! ቀየደቂቃው ፣ በከንቱ የሚሞተውን ወገናችንን መታደግ በራሱ የሚያሥመሠግን ተግባር ነው ።  ምንም የማያውቀው ምሥኪን ህዝብ ፀሎቱን ፈጣሪ ሰማው ። ” ነው ያልነው ። አብዛኛው ሠላም ወዳድ ህዝብና  ብዙዎቹ  ምሁራን ። በቀና ልቦና ይኽንን ነው ያሉት ። ( በበኩሌ ጦርነት መቆሙን ብቻ ሣይሆን ፍፁም ከአገራችን ቢጠፋ ደሥተኛ ነኝ ።  ” ሰው የሚገድልና የሚያሰቃይ ሤጣን ብቻ ነው ። ” ብዬ የማምን ሰው ነኝ ። ሤጣን ደግሞ በልዩ፣ልዩ መንገድ የሰውን አእምሮ ተቆጣጥሮ እንደ ሰው ፣ ሰው ሆኖ በሰዎች ህሊና ውሥጥ በያዳንዱ ሰው ይሁንታ የሚኖር ነው ። መጥፎ ና እኩይ ድርጊት ከየትም አይመጣም ። ሴጣን ከተጠናወተው ለበጎና ለሠናይ ምግባር ካልተገዛ አእምሮ እንጂ ! )

… ይኽንን ድንገታዊ የእርቅ ዜና ሥሰማ ግን ( ልብ በሉ ፤ ወያኔ ግብዓተ መሬቷ ሊፈፀም አንድ ሐሙሥ ሲቀረው የተደረገ የሠላም ሥምምነት ነው ። )     ” ከእንግዲህ  በሬ ወለደ ቢሉኝ አምናለሁ ። ” ነው ያልኩት ። ” The Impossible  is possible  . How the dead man Woking ? ” …  ። …

” ኩበት ሰምጦ ዲንጋይ ዋኘ ። አህያ  በቅጥር ጊቢ  ውሥጥ ተወስና  የውሻን ተግባር ፈፀመች ።  የቤት ፣የሠፈር  ጠባቂነት ላይ የተሰማራው  ውሻ ሣር ሊግጥ ና ሊያናፋ ፣ ወደ  ዳ ወጣ  ። ወተት ጠቆረ ። ኑግም ነጣ ። ” ቢሉኝ ከእንግዲህ በኋላ  አምናለሁ ። ነበር ያልኩት  ።  ነገሩ ሁሉ ፣ ” ድመት መንኩሳ ፣ ዓመሏን አትረሳ  ! ”   እንደሚሆን ግን አላጣሁትም ነበር ። ዛሬም እየሆነ ያለው ይኸው ነው ።

ዛሬ እየሆነ እያሥተዋልን ያለነው እውነት ግን ፣ዓይናችንን ለሠላም ብለን ሥንጨፍን  ፣ ከበፊቱ በተጠናከረ መልኩ  ዘመናዊ ቢላዋ እና ልዩ፣ልዪ ኃይልን የመሣል ተግባር ነው ። ኃይል በማደራጀት ና  በሥልጠና በማብቃት  ፤ ምናልባትም በጠላቶቻችን የታገዘ  ወታደራዊ ሥልጠና በማግኘት ለዳግማዊው  መብረቃዊ ጥቃት ወያኔ እየተዘጋጀች ሊሆን ይችላል ።  ይሁን እንጂ ይኽንን እኩይ የጥፋት ዕቅድ እንዳናውቅባቸው የሠላም ሥምምነት የጊዜ ማራዘሚያ ድራማ ትህነግ ከግብረ አበሮቹ ጋር እየተወነ  እንደሆነ የሚያጠራጥሩ ድርጊቶች አልፎ፣አልፎ ሲከወን እየታዘብን ነው ።

ለመሆኑ ፣ ” የኤርትራ ጦር ከራሱ ደንበር ይልቀቅ ፤ ካለቀቀ ሥምምነቱን አንተገብርም ። ” ማለት ምን ማለት ነው ? ” ህውሃት የትግራይ ክልል ምክር ቤትን ጠርታ መሠብሰቦ ምን መልዕክት ና ለማሥተላለፍ ፈልጋ ነው ? ‘ የሞትነውም እኛ ያለነው ና በጠብ መንጃ እየስፈራራን ህዝብን የምንመራው እኛ ነን  ። ” ማለቷ  ይሆንን ?  መከላከያን ያለ ደጀን ለማሥቀረት እና ተረት ለማድረግ ነው  እንዴ …” የኤርትራ ጦር ከድንበሩ  ይልቀቅ  ። ” እየተባለ በዘወርዋሬ የሚጮኸው ። የኢትዮጵያን መከላከያ አለአጋር ለማሥቀረት ተፈልጎ እንደሆነ የማይገባው ማነው ?

ወዳጄ ሆይ ! ሠላም !ሠላም ! የሚለውን  የማዘናጊያ ዘፈን አብረህ በማንጎራጎር አትዘናጋ  ። ወደድክም ጠላህም የተቀሩት ጥቂት እባቦች ጭንቅላታቸው ተቀጥቅጦ እሥካልሞቱ ጊዜ ደረስ የአማራና የአፋር  ልቂት እና የኢትዮጵያ መድማት  ቀጣይ እንደሆነም ተገንዘብ ። ለሚቀጥሉት አራት ወራት ወያኔ እፎይታን ካገኘች ለታአምር የሚበቃ ዘግናኝ ድርጊት መፈፀሞ አይቀርም ። ይልቁንስ ከኤርትራ ጦር ጋር እንደ አገር ተባብሮ የተቀናጀ የጦር ልምምድ ማድረግ የሚያዋጣ እና ጥሩው አማራጭ  መሆኑንን ተገንዘብ ። ወያኔ “በዓምበሉ “ አማካኝነት አሣልፎ የሰጠውን አገር ዛሬ በጠላትነት የሚመለከተው ከምዕራባውያን ጥቅም አንፃር መሆኑንም አትዘንጋ ። የዛሬው የወያኔ ዓምበልም የህውሓትን ማሊያ ለብሶ ለአሜሪካ ኢምፔሪያሊዝም እንደሚጫወት እወቅ ። የሚሊዮኑ ደሃ የትግራይ ወጣት ከንቱ ሞት ለእርሱ የሆሊውድ ፊልም ነው ። ( የሚያሳዝነው በዚህ እጅግ ዘመናዊ ዓለም እኛ እንደ ዲንጋይ ዘመን ህዝቧች በጭፍን እና በመንገኝነት ፤ በጉልበት መሪ የሆኑትን አላዋቂ ጥቂት ግለሰቦች መከተላችን ነው ። )

ወያኔዎች ለአሜሪካ  መንግሥት ባለሥልጣናት ፣ በሰጡት የወርቅ ገፀ በረከት በዘመናዊ መሣሪያ ብቻ ሣይሆን በዘመናዊ መንገድ  የትግራይን ልዩ ጦር እየሰለጠኑ እንደሚገኙ አጠራጣሪ ምልክቶች ከታዩ ይኽ እጅግ አደገኛውና ደግማዊ አደዋን ከሳች ሴራ እንደሚሆን ከወዲሁ ይወቁት   ። … ( የአሜሪካ ባለሥልጣናትን ጥቅም እንጂ ሌላ የሚገዛቸውም ሆነ የሚገዙለት ምድራዊኃይል እንደሌለ እናውቃለን ። በሱማሌያ የተዋረዱትም ነዳጇን አይተው ነው ። በዩክሬንም ይኽ የጥቅም ታሪክ ነው ከዘሌኒሥኪ ጋር እንዲወግኑ ያደረጋቸው ።   ሥጋ ባለበት በዛ ፣ አሞራ እንደሚሰባሰብ እወቅ ። )

ከትህነግ የጭራቅ መንገድ  ለመላቀቅም የኢትዮጵያ ህዝብ ያለው ምርጫ አንድና አንድ ነው ። አሁን እና ዛሬ እያባለን ያለውን የዘረኞች የከፋፍለህ ግዛ የፖለቲካ መንገዳችንን ወደ ሰውና ዜጋ ዘመናዊ የፖለቲካ ሥርዓት መቀየር ። ይኽንን ሥታደርግ ብቻ ነው ወያኔንን በአፍጢሙ የምትከሰክሰው  ። ይህንን ሥርዓት ካነበርን ፣ በአንድ ቀን የትግራይ ኗሪ ህዝብ ህውሃትን ታሪክ ያደርጋታል ።  እነዚህ ከ50 ዓመት በፊት ፣ በወቅቱ ባለው ነባራዊ ሁኔታ አሥገዳጅነት ህሊናቸው ውሥጥ በተሰነቀረ የጥላቻ መርዝ  የታመሙ ወያኔዎችና ርዝራዦቻቸው ፣ እሥከ አሥተሣሠባቸው ይጠፋሉ ። ይኽ ከፋፋይ ና የሰው እና የዜግነት ጠላት የሆነ የፐለቲካ ሥርዓት እሥካልተቀየረ  ጊዜ ድረስ ፤ በአገር ምድሩ ሤጣናዊ   ድርጊትና የድረሱልን ጩኸቱ  እንደማያባራ እወቁ ።

ነገ ተነገወዲያ ፣ የሰሜኑ እኩይ እና ከኢትዮጵያዊው ክቡሩ እና ጨዋ አስተሳሰብ ያፈነገጠ  እና ኃይማኖታዊ ሥነምግባርን  የጣሰ  ድርጊት በሁሉም ክልሎችም እጅግ መስፋፋቱም አይቀርም ። ( የዮናታንም ( The devils advocacy የተባለ የሆሊውድ ፊልም ዓይነት ) ሥብከት ይኽንኑ የተቀናጀ ኢትዮጵያን የማፈራረስ አጀንዳ የሚያመለክት ነው ብዬ አሥባለሁ ። ማንም እየተነሳ ለምን “ በዋቄ ፈታ “ ታምናለህ ሊለኝ አይችልም ። ምን አገባው ? እያንዳንዱ የኃይማኖት አሥተሣሠብ ከህግ ተቃራኒ እሥካልሆነ ጊዜ ድረስ ይከበራል   ። የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትና አሥተምህሮም በኢትዮጵያ ትልቁን የህዝብ ቁጥር የያዘ ነውና  ሊከበር ይገባዋል ። አንድአንዱ ሰባኪ አወቅህ ፣ አወቅህ ሲባል “ እኔ ኢየሱስ ነኝ ። “ እንደሚል በኢትዮጵያ የኃይማኖት  ታሪክ ተደጋግሞ መታየቱንም አሥታውሱ ። በግሌ “ አዩም ሆነ ዮናታን ) ለእኔ   ተራ ሟቾች  ናቸው ። ከሞቱ በኋላ  የሚፈጠረውን   የሲኦልና የገነቱን ቅጣት  ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያቅላቸው ። …

እና ዛሬ ከጎጠኞች  ጋር ተዳብለወ በኃይማኖት ሥም ህዝብን የሚከፋፍሉ የነማን ቅጥረኞች እንደሆኑ የታወቀ ነው ። እሥቲ ለልማት እና ለደሃው ህዝብ እንሰራለን ካሉ በሚሊዮን የሚቆጠርን ወጣት ወደ ሥራ የሚያሰማሩ የተለያዩ ለአገር የሚበጁ ፋብሪካዎችን በአገራችን እንዲገነቡ ለወሬ ብቻ የሚደጉሟቸውን ፈረንጆች ይማፀኑ  ። አገር የምትገነባው እኮ ፀሎት ከሥራ ጋር ሲጣመር እንጂ ቸርች ውሥጥ ዝንጥ ብሎ በርዕቱ አንደበት በማውራት  አይደለም ።…

ዛሬ እና አሁን ፣ መርዘኞቹም ሆነ መርዙ ሳይኖር  ፤ በጥቅም የተሣሠሩ ፣ መሞታቸውን የዘነጉ ዘረኞች ና ጎጠኞች ከ 50 ዓመት በፊት    በሚሰቃዩበት ህመም እየተሰቃዩ ነው።   እነዚህ   ህሊናቸው የታመመ  ፖለቲከኞች እና ደቀመዝሙሮቻቸው ፤ ቢያንስ  በተፈጥሮ ሞት   ከምድሪቱ እሥካልጠፉ ጊዜ ድረስ ዜጎች አጭርና ጣፋጪ መሆን የሚገባትን ህይወታቸውን በስቃይና በሰቆቃ መኖራቸውን ይቀጥላሉ ።

በበኩሌ እነዚህ እብድ ፕለቲከኞች ከኢትዮጵያ ጥርግርግ አድርጎ ፈጣሪ እንዲያጠፋቸው እና በአገራችን የዜጎች ሰብዓዋ መብት እና የዴሞክራሲ መብት ተከብሮ ፤ ፍትህ ለሁሉም እኩል ተዳርሶ … ህግም በአገራችን የሁሉም የበላይ ሆኖ ፣ የሁሉም ሰው መብት በቋነቋ ሥም ሳይረገጥ ዜጋ በአገሩ እንዳሻው  ተዞዙሮ በመሥራት ህይወቱን አጣፍጦ ፣ለትውልዱም ጥሪት አፍርቶ የሚሞትበት መልካም ሥርዓት እንዲመጣ እፀልያለሁ ። …

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ለዶ/ር አብይና ብልጽግና ፓርቲ እጅግ አሰቸኳይ የዜጎች እልቂት መፍትሄ መልክት

Next Story

የአማራውን ሕዝብ እንባ ጠባቂዎች ከጽንፈኛው ኦነግ ሸኔ በማመሳሰል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የተሰነዘረውን የእብሪት ዛቻ በመቃወም የተሰጠ መግለጫና የትግል ጥሪ

Go toTop