አዳነች አቤቤ በገነት ዘውዴ የዕብሪት መንገድ መሄድ

December 8, 2022

ብሃራቸውን ሳንቆጥር በርቱ ያልናቸው ከንቲባ ወ/ሮ ገነት ዘውዴን በሚያስንቅ የትምህርት ፖሊሲ ህጻናቱን ሊቀጡ ብቅ ብለዋል።

* ጥቂት የማይባል አዲስአበቤ ብሄር ሳይቆጥር የመጡበትን ድርጅት ሳይመትር ታከለ ኡማን – ታኬ ፣ አዳነች አበቤንም እንዲሁ እያቆላመጠ በርቱ ብሏል ጅምራቸው ይሳካ ዘንድ አይዟችሁ ሲል አበረታቷል።

* የአዲስአበባ ነዋሪ የኑሮ ውድነቱ ምሬቱን ጣሪያ ባደረሰበት ወቅት ከከንቲባ አዳነች አቤቤ የሚጠብቀው የተቀናጀ የዋጋ ማረጋጊያ ስርአት ፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፣ ፈር የለቀቀውን መንግስታዊ ሌብነት የማስታገሻ እርምጃዎች ነበር።

* አለመታደል ሆኖ የህዝብ ጥያቄ ሌላ የመንግስት ምላሽ እዚያ ግድም ሆኗል። የከተማው ህዝብ ሳይወያይበት ይሁንታ ሳይሰጥ የኦሮሚያ ክልል ባንዲራና ክልላዊ መዝሙር ለእነ አዳነች የቅድሚያ ቅድሚያ ሆኗል። ይሄ ጉዳይ ሊውል ሊያድር ህዝብ መክሮ ይሁንታ ሊሰጥበት የሚችል አጣዳፊ ያልሆነ አጃንዳ ነው።

* ዕድሜህ ይጠር ያለው የብልጽግና መንግስት የዛሬ አራት አመት በመቶ ሺዎች ሆኖ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በአደባባይ ያነገሰው ከተሜ ላይ ዘመቻ ሊጀምር ዳር ዳር እያለ ያለ ይመስላል ። የብሄር ፖለቲካን ከዜግነት መብቶች ጋር ያስታርቃል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ብልጽግና ገና የትግራዩ ጦርነት ቁስል ሳይጠግ ፣ የኦሮሚያ ትርምስ መልክ ሳይይዝ ከሰባት ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች ያሉባት አዲስአበባ ላይ የብሄር ጦርነት ሊከፍት እየተቅበዘበዘ ነው።

* በፓርቲ ጉልበቱ ዕብሪት የወጠረው ህወሃት ከከተሜ ጋር ጸብ እንደማያዋጣው ያወቀው በምርጫ 97 ሸገር ላይ በዜሮ ከተሸኘ በኃላ ነው። የአዲስአበባን ነዋሪ እንኳን የሌቦች ስብስቡ ብልጽግና በድርጅታዊ ዲሲፒሊኑ የማይታማው ህወሃትም አንገት አላስደፋውም !

* አዳነች አቤቤ በገነት ዘውዴ የዕብሪት መንገድ መሄድ ከመረጡ ውጤቱን ብዙም ሳይቆዩ ማየታቸው አይቀርም። ህዝብን በጠላትነት ፈርጆ አንገቱን ሊያስደፋ የሞከረ የትኛውም ፖለቲከኛ ተሳክቶለት አያውቅም !

Habtamu As

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ስለ ወለጋ ጭ.ፍጫፋ እውነቱን ተናገሩ | የአማራና የኦሮሞ ግ.ጭ.ት አይደለም | ኢዜማ

Next Story

በሴቶች ላይ የሚደርስ የኃይል ጥቃት በአስቸኳይ ይቁም – ከአኒሳ አብዱላሂ

Go toTop