ጽርሐ ጽዮን እሮጣለሁ” መንፈሳዊ ዓላማ ያለው የጎዳና ላይ ሩጫ በባሕር ዳር ከተማ ተካሄደ

December 4, 2022
መነሻውን ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን በማድረግ መድረሻውን ጽርሐ ጽዮን ቅድስት ማሪያም አንድነት ገዳም ያደረገው ሩጫ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ጨምሮ ታላላቅ የአብያተ ክርስቲያኗ አባቶች፣ የመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች እና ሕዝበ ክርስቲያኑ ተሳትፈውበታል።
በመርሐ ግብሩ ላይ አትሌት ሻለቃ ኀይሌ ገብረ ሥላሴ በክብር እንግድነት ተገኝቷል።
በሩጫው ከሴቶች ገንዘቤ ጋረድ ፤ ከወንዶች ያረጋል ቀሬ ፤
ከአካል ጉዳተኞች በወንዶች ሞገስ እስከዚያው እንዲሁም
በሴቶች እናትሁን ዓለም አሸናፊ መሆናቸውን አሚኮ የዘገበ ሲሆን ከአረጋውያን ደግሞ በወንዶች አደመ መንግሥቱ
በሴቶች ደግሞ ትነበብ ታደለ መንፈሳዊ ሩጫውን በአሸናፊነት አጠናቅቀዋል።
መንፈሳዊ ሩጫው ለጽርሐ ጽዮን ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም እና በውስጡ ለተካተቱ ዘርፈ ብዙ መንፈሳዊ ፕሮጀክቶች ገቢ የማሰባሰብ ዓላማ ያለው መሆኑም ታውቋል።
አዲስ አድማስ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የዐማራ የህልውና ትግል መርህ የትግል ጥሪ

Next Story

‹‹መዋቅራዊ ማሻሻያ መርሃ-ግብር!!!›› ከዓለም ባንክና አይኤምኤፍ ሆድቃ፣ ዶላር ፍለጋ በጨረቃ!!! (ክፍል 2) – ሚሊዮን ዘአማኑኤል

Go toTop