በካናዳ የኦንታሪዎ  ክፍለ ሃገር ለማዘጋጃ ቤት የከንቲባዎችና ካውንስለሮች ሕዝባዊ ምርጫ ትወልደ ኢትይዮጵያዊው  አቶ ንጉሴ ዓዳሙ አሸናፊ ሆነዋል  

October 24, 2022

በካናዳ የኦንታሪዎ  ክፍለ ሃገር ለማዘጋጃ ቤት የከንቲባዎችና ካውንስለሮች(councillors) ሕዝባዊ ምርጫ ዛሬ October 24, 2022 ተካሂዷል። በዚሕ የምርጫ ውድድር የቤሪ ከተማ ቀቤሌ -6 ( Ward- 6) የተወዳደረው ትወልደ ኢትይዮጵያዊው  አቶ ንጉሴ ዓዳሙ  በከፍተኛ ብልጫ አሸንፎ የቤሪ ቀበሌ-6 (ward-6) ካውንስለር ሆኖ ተመርጧል።

ምርጫው ታሪካዊ ሲሆን በካናዳ ተወልደው  ላደጉ ልጆቻችን መሌና የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ካውንስለር በካናዳ ያደርገዋል። ከዚህ በተጨማሪ በአብማ ማሪያም ቀበሌ፤ ደብረ ማርቆስ ከተማ፤ ኢትዮጵያ ተወልዶ የካናዳ ቀበሌ ካውንስለር መሆን ምንኛ ደስይላል። በዴሞክራሲ እጦት ተሳዶ ካሃገሩ የወጣው ንጉሴ ዴሞክራሲ ባላበት ሃገር መመረጥ መቻሉ ሁሉን ኢትዮጵያዊ ያኮራ ነው ብለን እናምናለን።

ስለሆነም አቶ ንጉሴን፤ ባለቤቱን ሐናንና ሁለት ልጆቹን እንኳን ደስያላችሁ እንላለ።

ሰማነህ ታምራት ጀመረ

የንጉሴ የምርጫ ዘመቻ አስተባባሪ ቡድን ሊቀመንበር።

Monday October 24, 2022

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የክፉዎች ፍልሰት ይሁን (Let Exodus of Evil be) – ሰማነህ ታ. ጀመረ-ዖታዋ፤ ካናዳ፤

Next Story

ዘመን ተሻጋሪና እውነታን መስካሪ የአማራ ህዝብ እንጉርጉሮወች አጭር ቅንጫቢ (እውነቱ ቢሆን)

Go toTop