መንግሥት መንገደኞች ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ ከተማ የመግባት መብታቸውን እንዲያስከብር – ኢሰመጉ

August 12, 2022
ያለፉትን አራት ዓመታት የመራውን ግለሰብ አብይ አህመድን ብንመለከት በሕዝብና በአገር ስም የሚሰጠውንም ሆነ በብድርና በእርዳታ የሚገኘውን ገንዘብ እንደ ግል ሃብቱ ሲበትን፣ለምን  እንዲህ ይሆናል ብለው የጠዬቁትን ምን አገባችሁ እያለ ሲሳደብና ሲያንጓጥጥ ማዬቱ የተለመደ ነው

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) መንግሥት መንገደኞች ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ ከተማ የመግባት መብታቸውን እንዲያስከብር እና በከተማዋ ዙሪያ ባሉ ፍተሻ ኬላዎች ላይ መንገደኞችን የሚያጉላሉ፣ የሚደበድቡና የሚያስሩ እንዲሁም ከመንገደኞች ጉቦ የሚቀበሉ የጸጥታ ኃይል አባላትን በሕግ እንዲጠይቅ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። ኢሰመጉ ከአንድ ወር ወዲህ ከአማራ ክልል በተሽከርካሪ ወደ አዲስ አበባ የተጓዙ መንገደኞች ከከተማዋ ዙሪያ የፍተሻ ኬላዎች ላይ ጸጥታ ኃይሎች መታወቂያቸው እያዩ ወደመጡበት እየመለሷቸው እና ፍተሻ ኬላዎች ላይ እያጉላሏቸው መሆኑን መረጃ ደርሶኛል ብሏል።

ኢሰመጉ መንገደኞች ወደ ከተማዋ እንዳይገቡና እንዲንገላቱ እየተደረጉ ያሉት፣ በከተማዋ ዙሪያ ባሉት ሸኖ፣ አለልቱ፣ በኪ፣ ሰንዳፋ እና ለገጣፎ የፍተሻ ኬላዎች ላይ መሆኑን በመግለጫው ጠቅሷል። ጸጥታ ኃይሎች መንገደኞችን የሚያሳልፉት የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ክልል መታወቂያ የያዙ ከሆኑ ብቻ እንደሆነ የገለጸው ድርጅቱ፣ ባንዳንድ የፍተሻ ኬላዎች ላይ መንገደኞችን ለማሳለፍ ጸጥታ ኃይሎች ጉቦ እንደሚጠይቁ መረጃ እንዳለው ጠቁሟል።
ነሐሴ 4 ላይ ከወልድያ-አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ሙሉ በሙሉ ተዘግቶ ነበር ያለው ኢሰመጉ፣ በነጋታው ግን መንገዱ መከፈቱን አረጋግጫለሁ ብሏል። ኢሰመጉ ነሐሴ 3 ላይ ሰላም ሚንስቴር እና ትራንስፖርት ሚንስቴር በጉዳዩ ላይ በጽሁፍ ማብራሪያ እንዲሰጡት መጠየቁንም ጠቅሷል። ሆኖም ከጉዳዩ አሳሳቢነት አንጻር፣ ከሚንስቴሮቹ የጠየቀውን የጽሁፍ ማብራሪያ እስኪያገኝ ሳይጠብቅ፣ ይህን መግለጫ ለማውጣት መገደዱን ድርጅቱ ጨምሮ ገልጧል። [ዋዜማ ራዲዮ]

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የኢትዮጵያ ካሽሚር የሆነው የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ሊፈታ የሚችለው በወታደራዊ ሃይል ብልጫ ነው!!!

Next Story

እሺ የጉራጌ ዞን ክልል ሆነ እንበል:: ከዛስ? – ብርሃኑ ዘርጋው

Go toTop