የስፔን ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ ጉብኝትን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

July 26, 2022

ከኤምኤስኤፍ ስፔን ፕሬዝዳንት ከወ/ሮ ፓውላ ጊል የተሰጠ

ጁላይ 26 2022— በዚህ ሳምንት መጨረሻ የስድስት ቀናት የአዲስ አበባን ጉብኝቴን ሳጠናቅቅ በጣም ተስፋ አስቆራጭ ነው የተሰማኝ። ጁን 24 ቀን 2021 በትግራይ ክልል ሶስቱ ባልደረቦቻችን ከተገደሉ ከአንድ አመት በኋላ፣ ሀዘኑን ቤተሰቦቻቸውን አግኝቼ በጉዳዩ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት ጋር የምናደርገውን ውይይት እንቀጥላለን የሚል ተስፋ ነበረኝ።

ይሁን እንጂ ትግራይን እንድጎበኝ ከባለሥልጣናት ፈቃድ አልተሰጠኝም ነበር፡  ይህ ማለት በግፍ የተገደሉትን የቴድሮስ እና የዮሐንስን ቤተሰቦች፣ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉትን ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ባልደረቦቻችንን ህልፈተ ህይወት መዘከር አልችልም ወይም የኤምኤስኤፍ የውስጥ ግምገማ ሂደት ለቤተሰቦቹ ማሳወቅ አልችልም ማለት ነው። ስለ ክስተቱ ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ጥያቄ ባቀርብም በሦስቱ ሠራተኞቻችን ግድያ ላይ ባደረጉት ምርመራ ዙሪያ ውይይቱን ለመቀጠል ከፌዴራል መንግሥት ተወካዮች ጋር መገናኘት አልቻልኩም፡፡

ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ከአንድ አመት በላይ ስንነጋገር ከቆየን በኋላ፣ በዚያን ወቅት በባልደረቦቻችን ላይ ስለደረሰው ነገር ምንም አይነት ተአማኒነት ያለው መልስ ባለማግኘታችን አዝነናል። ጉብኝቴ  ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስት ጋር ባለን ግንኙነት ወሳኝ እርምጃ እንዲሆን ታስቦ ነበር፣ እናም በቀጣይ እርምጃዎቻችን ላይ የምናሰላስልበት ጊዜ አሁን ነው። የምንችለውን መንገድ ሁሉ በመጠቀም በባልደረቦቻችን ላይ ለደረሰው ግድያ ተጠያቂነትን ለማምጣት ጥረታችንን እንቀጥላለን።

ከ20 ወራት ግጭት በኋላ፣ አሁን እየጨመረ ከሚሄደው የምግብ ዋስትና እጦት እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ጋር ተዳምሮ፣ ህይወት አድን የህክምና አገልግሎት ሳያገኙ ህዝቦች የሚያጋጥሟቸው አስጨናቂ  ሁኔታዎች በጣም ያሳስበኛል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ከሞፈር ያዥ ወደ ጠመንጃ ያዥ! የበጋ የመስኖ ስንዴ ፋና ወጊዎች የወርቅ ሜዳልያ ሊሸለሙ ይገባል!›› – ሚሊዮን ዘአማኑኤል

Next Story

ለነፃነታችንና እየተጣሰ ላለው የፍትህ ስርአት ማንኛውንም ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ነን ሲሉ 14ቱ የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻች አባላት ገለፁ

Go toTop