የአብይ መንግስት የተፈጸመው ጄኖሳይድ እየሆነ ያንን ለመሸፋፈን፣ የሞቱትን ቁጥር በመቀነስ የነዚህ ሰዎች ወንጀልን ለማሳነስ በመሞከር፣ የችግሩን አስከፊነት ለመደባበስ ነው እየሰራ ያለው፡፡
አራት ኪሎ ቁርጠኛ የሆነ፣ የሕዝብ ስቃይ የሚሰማው መንግስት ቢኖር ኖሮ ፣ ለችግኝ ተከላ ያለውን ቁርጠኝነት አንድ አስረኛ እንኳን፣ “ሰው መሞት የለበትም” የሚል ቁርጠኝነት ቢኖረው ይሄ ሁሉ ጄኖሳይድ አይኖርም ነበር፡፡
ጭፍጨፋው ነገም፣ ከሳምንት በኋላም ይቀጥላል፡፡ እነ አብይና ኦህዴዶች የፌዴራል መንግስቱን እስከተቆጣጠሩ ድረስ ፣ በሩዋንዳስ ቱትሲዎች ካክሮች(ትንኝ) ተብለው ይጨፈጨፉ እንደነበረው፣ አማራው በኦሮሞ ክል መጤ፣ ሰፋሪ፣ ነፍጠኛ ተብሎ መጨፍጨፉ ይቀጥላል፡፡
አብይ አህመድ የኦሮሞ ጽንፈኛ ታጣቂዎችን አደብ ከማስገዛት፣ ሰራዊቱን አማራ ክልል ልኮ ሰላማዊ ዜጎች ላይ፣ ፋኖ ላይ ነው ጦርነት የከፈተው፡፡
ወገኖች ከዚህ በኋላ አፈሙዙን ወደ አራት ኪሎ በማድረግ ነው በኦሮሞ ክልል ያለውን አማራውንም ሆነ ሌላውን ማህበረሰብ ማዳን የሚቻለው፡፡