![](http://amharic-zehabesha.com/wp-content/uploads/2022/06/Abiy-Liar.jpg)
አብይ አህመድ በፓርላማ ንግግራቸው ላይ ቁጣ በተሞላበት አነጋገር ለምን በኦሮሚኛ ተዘመረ አላችሁ ብለው ደንፍተዋል ።ሆኖም ግን እሳችው አደባብሰው ፣ሸፍነው ያለፉት ሀስት ጉዳይ አለ ። በአዲስ አበባ ውሰጥ ፣ ከድሮ ጀምሮ በጃልሜዳም ጥምቅት ባህል ላይ ፣እንዲሁም በሙዚቃም አለም ላይ ኦሮሞኛ ሲዘፈን ኖሯል ።ችግሩ የኦሮሞኛ መዝሙሩ ላይ ሳይሆን ፣ ችግሩ የኦሮሞ ሰንደቅ አርማው ዝማሬ ላይ ነው። አንድ ሀገር አንድ ባንዲራ አንድ መዝሙር ከሌላት ምኑን አንድ ሆንን።
የኦሮሞ ተማሪዎች ከሌሎች ኢትዮጵያኖች የተለዩ ሆነው እንዲያድጉ ፣ ኢትዮጵያዊነታችውን ትተው ኦሮሞነታቸውን እንዲያጠብቁ በመንግስት ወጪ እየታገዙ ይገኛሉ። ኢትዮጵያዊ ናሺናሊዝምን ደምስሶ ብሄርተኛን ማጋነን መጨረሻው ውድቀት መሆኑን እንደ ዶ/ር ደረጃ ትምህርታቸው ሊረዱት ይገባ ነበር ። የሚያሳዝነው ፣የኦሮሞ ተማሪዎች ፣ ከሊሴ ተማሪዎች፣ ከፈረንሳይ ፣እንዲሁም ከኢንግሊዝ ተማሪዎች ጋር ማነጻጸራቸው ሌላው አሳዛኝ እና እጅግ አሳሳቢ ጉዳይም ነው። እንግሊዞች፣ ፈረንሳዮች፣ ጣሊያኖች በራሳቸው ቋንቋ ፣ በራሳችው ባንዲራ ስር መዘመራቸው ከኦሮሞ ተማሪዎች ጋር ምን አገናኘው ? ሌላው የሚገርመው ፣ ዶ/ር አብይ በመከላከያ ተገኝተው ከዘረ ፓለቲካ ውጡ ፣ በብሂር አትመኑ እያሉ ይደሶኩሩና ፣ የኢትዮጵያ ግማሽ ሕዝብ ቁጥር ነው የሚሉትን ኦሮሞን ግን ብሄርተኛ ለማድረግ ሲጥሩ ፣ሲያበረታቱ ይስተውላሉ ። ሌላው ፣ ዶ/ር አብይ በአዲስ አበብ ዙሪያ ብለው ፣ ሸዋ የኦሮሞ እንብርት ማድረጋቸው ነው። ስልጣን ላይ ስላሉ እንጂ አዲስ አበባም የእሮሞ እንብርት ናት ለማለት ወደኋላ የሚሉ አይመስለኛም ።
እንግዲህ በእሮሞኛ እንብርት ማለት ምን እንደሆነ እንቆቅልሽ የሆነብን ብዙ አማራዎች አለን ። እንበርት የምናውቀው መሀል ላይ ያለ እንጂ አፍንጫ እንብርት ሆኖ አያውቅም ። አዲስ አበባ ስትሆን ፣ ሸዋ ለአሩሲ አጎራባች ፣ለወለጋ በደቡብ አጎራባች እንጂ ሸዋ የኦሮሚያ /የኦሮሞ |እንብርት ልትሆን ልትሆን አትችልም ። በ1983 ያለ አግባር በህወህት እና በኦነግ ስምምነት የተነጠቀ መሬት ነው። ወልቃይት /ራዕያ ፣ ሸዋ ና መተከል ወደ አማራ ግዛታቸው ሊመለሱ ይገባል ፣ ዶ/ር አብይ እንብርታቸውን አሩሲ ላይ አልያም ወለጋ ሄደው ቢፈልጉ መልካም ነው።
Shewa Amhara
https://zehabesha.com/ethiopia-more-than-200-ethnic-amhara-have-been-killed-in-an-attack-in-the-countrys-oromia-region/