- አሁን አማራ ተብለው በአማራ ኮታ ከገቡት በላይ በረከት ስምዖን እንደውም የበለጠ አማራ ነው። እስኪ አማራ ነን ካሉ ይምጡና ባህርዳር ላይ አማራ ነን ብለው ያስተዳድሩ?
- “ብልፅግና ሲመሠረት የተስማማንበት በየክልሉ ያሉ አማራዎች የመወከል፣ የመምረጥ እና መመረጥ ጥያቄ ፡ በተግባር ወደ መኖር አለመኖር ጥያቄ ተቀይሯል። “
- በብልጽግና ጉባኤ ላይ ሁሉም ክልሎች ያስጠቆሙትን ሁሉንም ያሣለፉ ሲሆን አማራ ግን ከተጠቆሙት 55 ሰዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሆኑት እንዳያልፉ ተደርገዋል። ጭራሽ ከጉባኤ ውጭ 7ሰዎችን ጨመሩ። በጉባኤው ሰርጎ ገቦችን እንመነጥራለን ብለው የአማራ ተወካዮችን መንጥረዋል። ስለዚህ ሰርጎ ገቦቹ አማራዎች ናቸው ማለት ነው።
- እስከዛሬ በማይታወቅ ኢህጋዊ አካሄድ አንድ ሰው ስድስትና ስምንት ሰዎችን እንዲጠቁም እድል ይሰጠው ነበር። ይሄም ቀድሞ የተሰራ ይመስላል።
- አሁን ላይ የተመረጡት ያጨበጨቡት ብቻ ናቸው። ያኔ እነ መለስ እነ በረከት በነበሩ ሰአት “አብዮታዊ ዴሞክራሲ ለዚህች አገር አጥፊ ነው” ስል የረገሙኝ ዛሬ የለውጥ መሪ ነን ብለው ከመጣው ጋር እያጨበጨቡ ነው።
- ያኔ በለውጡ የተስማማንቤቸው የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች አንዳቸውም አልተመለሱም፣ ህገ መንግስቱን ጨምሮ።…”