ከወደ አስመራ ብቅ እያለ የሚለው ንፍስ ጥሩም አይደለም። ኢሳያስ አፈወርቂ እንዲህ በቀላሉ በኢትዮጵያውያን ላይ ተስፍ የሚቆርጥ መሪ አይመስለኝም ነበር። አሁን ነገሮች ወደ መቀዛቀዝ እየሄዱ ነው። የአዲስ አበባ ባለስልጣናት ወደ ኢሳያስ የሚጫኗቸው የአረንጓዴ ደውል ምልክቶች በአስመራ ሹማምንቶ በኩል ችላ ተብለዋል።
አስመራ በአዲስ አበባ ፖለቲካ ላይ እጆቿን አስገብታ አበላሽታለች ከመባል፣ እስከ ትግራይ ድረስ ገብታ ጆኖሳይድ ፈፅማለች የሚል ክስ ይቀርብባታል። የባድመ መሬትን በጀ አስገብቻለሁ ማነው የሚወስደው ህወሓት ሆይ ስረአት ያዝ እቢ ካልክ መናጢው የሻቢያ ወታደር መልሱ ከባድ መሆኑን ታውቃለህ እያለች በማስፈራራት መሬቱን በጇ ቁጥጥር ስር አድርጋው ትገኛለች። ወታደሮቿም ባድመ የሚል ቢራ አሰርተው እየጨለጡ ሲጨፍሩበት ይታያሉ።
በየቀኑ እያሽቆለቆለ የመጣው የአስመራ ውለታ ቢስነት በፌደራል መንግስቱ ጭምር እየተተገበረ ቆይቷል የሚል እምነት አድሮባታል። ኤርትራ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ የተፀፈመውን ክህደት አስመልክታ ህወሓትን በመግታት ረገድ አሁን ያለው የአብይ አሕመድ መንግስት እንዲኖር አድርጋለች። የአዲስ አበባ መጣጥፎች ያላበሩበት ይህ ታሪክ በኤርትራ መንግስት ግን አንድ እርምጃ ተብሎ ተይዟል። ስንት መሰዋትነት የተከፈለበት የሰሜኑ ጦርነት ያለምንም ግብ በዜሮ ሲጠናቀቅ፣ ትናንት ወዳጅ ተብላ ከቦሮ ሲደበደብላት የከረመች ኤርትራ አሁን ጥላት ናት፣ የሚል ክስ ቀርቦባታል። በአቋመ ፅኑነቱ የሚታወቀው ኢሳያስ አፈወርቂ እንዲህ አይነት ክህደት የሚፈፀመብት አልመሰለው ነበር። አሁን ኤርትራ ለኢትዮጵያ የዋለችው እያንዳንዱ ነገር ሁሉ ገደል ተከቶ እንደውም ከምዕራባውያን መንግሥት የማዕቀብ ናዳ ሲወርድባት ከርማ በቀላሉ ውላታ ቢስ ከሀዲ ወራሪ በጥባጭ የሚል ወቀሳን ተሸክማ ለብቻ መምከር ጀምራለች።
.
ለግዜው አምባሳደር አያሻኝም፣ ምናልባት የተሻለ ነገር ይመጣ ከሆነ ለማየት አዲስ ጉዳይ አስፈፃሚ አስቀምጣለሁ፣ በክብር ያስቀመጥኩትን፣ አምባሳደር ግን ወደ አስመራ ይመለስልኝ ብላ ጠርተዋለች። አምባሳደሩ ግን የስልጣን ጊዜውን አጠናቆ ሄደ ተብሎ በአዲስ አበባ ጋዜጠኞች ቢዘገብለትም ነገሮች ግን እንደዛ አይደሉም።
ከዛ ይልቅ አስመራ ለዋልኩት ውለታ በግልፅ ልመሰገን ይገባኛል የአብይ አሕመድ መንግስት ቃሉን አልጠበቀልኝም የሚል ወቀሳ ስታቀርብ ቆይታለች። አሁን ላይ ግን ለቀባህር ሰላይዎች የተረፈው የአዲስ አበባና የአስመራ ፍቅር ሽውታ መቶታል። ሰላም ሰላም ለኢትዮ ኤርትራ በሚል ሙዚቃ የሰላም ቅኔዎችን ዘምረን እንደታረቅነው ሁሉ፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድም የኖቤል ሽልማታቸውን ያነሱበት እርቅ ወደ ፀብ ላለመቀየሩ ዋስትና የለውም ይላል የሱዳኑ ጋዜጣ አል አለሚ በረጅሙ ትንታኔው ላይ።
በኢትዮጵያ መንግስት በኩል የአስመራና የአዲስ አበባ ግንኙነትን በተመለከተ እስካሁን ምንም አይነት ማብራሪያ አልተሰጠበትም።
ሱሌማን አብደላ