ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት፣ በአዲስ አበባ ካሉት የመንግሥት ትምህርት ቤቶች መካከል በአንዱ በህገ ወጥ መንገድ ተሰቅሎ የሚገኘው የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ ዓላማ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ አበባ ውስጥ ባሉ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ጠዋት ጠዋት ተማሪዎች ተሰባስበው መዝሙር በሚያሰሙበት ጊዜ፣በአንድ ረድፍ የኦሮሞ ተማሪዎች ከኦሮሚያ ሰንደቅ ዓላማ ፊት ቆመው የኦሮሚያ ክልል መዝሙርን ፣ በሌላ ረድፍ ሌሎች ተማሪዎች ከኢትዮጵያ ፊት ሰንደቅ ዓላማ ፊት ቆመው የኢትዮጵያን ብሔራዊ መዝሙርን እየዘመሩ ይገኛሉ፡፡ ይህ አካሄድ ፍፁም አደገኛ እና ሕገ ወጥ መሆኑን አብዛኛው የከተማዋ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡
እንደሚታወቀው፣ የአዲስ አበባ ሕዝብ ከአስተሳሰቡና ከፍላጎቱ ውጭ የተጫነበት የከተማዋ አስተዳደር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየሄደበት ያለው መንገድ በእጅጉ እያሳሰበው ይገኛል፡፡ በተለይ የገዥው ፓርቲ ከህወሓት ጋር የመታረቅ ተስፋው እየለመለመ በሄደ ቁጥር፣ በከተማዋ ነዋሪ ላይ የሚያደርገው ዘረኛ ተፅዕኖ እየበረታ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ዋነኛ መገለጫዎች መካከል፣ በአዲስ አበባ የመንግሥት ት/ቤቶች የኦሮሚያ ክልል ባንዲራን መስቀል፣ ትክክለኛውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ህገ-ወጥ ነው ብሎ ክልከላ ማድረግ፣ የአዲስ አበባ ወጣቶችን እንደ ጠላት በማየት በአፈሳ ለጅምላ እስር መዳረግ፣ በከተማዋ መስተዳድር ውስጥ ያለው ዘረኝነት መባባስ ይገኙበታል፡፡
#ኢትዮጵያ
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ
·