የኢዜማ መሪዎች የብልጽግና መንግስትን አካሄድ በመቃወም ለውጡ ተቀልብሷል ሲሉ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል

March 20, 2022
የኢዜማ መሪዎች የብልጽግና መንግስትን አካሄድ በመቃወም ለውጡ ተቀልብሷል ሲሉ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)፣ የአዲስ አበባ ዞን ማስተባበሪያ ምክር ቤት ያዘጋጀው የውይይት መርሐ ግብር፣ የኢዜማ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ትላንት መጋቢት 10/ 2014 ዓ.ም. በመስፍን ወልደማርያም (ፕ/ር) አዳራሽ ተካሄደ:: በውይይቱም የኢዜማ ሊቀመንበር የሺዋስ አሰፋ፣ ምክትል መሪ አንዱዓለም አራጌ እና ዋና ፀሐፊ አበበ አካሉ፣ ከወረዳዎች ሊቀመናብርት እና ድርጅት ጉዳይ ተወካዮች ለተነሱ ድርጅታዊ እና ወቅታዊ የፖለቲካ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል:: መርሐ ግብሩን የኢዜማ አዲስ አበባ ዞን ማስተባበሪያ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ መርተውታል!
በጦርነቱ ወቅት ተደራጅቶ ከተማውን የጠበቀ ወጣት ፖሊስ ሆኖ ከተማውን የማይጠብቅበት ምክንያት የለም። እድሉ ለከተማው ወጣት መሰጠት አለበት። እስከዛሬ መንግስት ከጠረጴዛ ላይ ብርጭቆ አንስቶ ለመስበር እንደሚንደረደር ህፃን፣ ኢዜማ ደግሞ በርጭቆውን ከህፃኑ እጅ ተቀብሎ ለመዳን የሚደረግ አይነት መሳቀቅ ነበር።መንግስት ለሚያደርገው ሃላፊነት የጎደለው ተገባር እኛ እንሳቀቅ ነበር። አንድም ቀን የለውጥ ሃይል የተባለው መንግስት ለውጡን ለመቀልበስ ምክንያት ይሆናል ብለን አስበን አናውቅም ነበር።
አቶ የሺዋስ አሰፋ || የኢዜማ ሊቀመንበር
ኢህአዴግን ያንበረከከ የህዝብ ትግል የአህአደግን የልጅ ልጆች ማሸነፍ አያቅተውም። አሁን ያለን አካሄድ ሀገራችንም ፓርቲም አያድንም። የሚያሳዝነው ለአገር ብለን የከፈልነው ዋጋ በህዝብ እንደተለጣፊ በብልፅግና እንደሞኝነት መቆጠሩ ብቻ አይደለም፣ እንዳትፈርስ ብለን ተለጣፊ የተባልንላትና በወቅቱ ገዢዎች እንደሞኝ የተቆጠርንባት አገራችንም የከፋ ችግር ላይ መውደቋ ነው።
አንዱአለም አራጌ(ቀጣዩ የኢዜማ መሪ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ሃላፊነትና ተጠያቂነት – ጠገናው ጎሹ

Next Story

ለውጥ ሳይኖር ተቀለበሰ ማለት የለውጥን ትርጉም አለማወቅ ነው !

Go toTop