የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ቀጠና ኃላፊ በደሴ ከተማ ተደበደቡ

March 31, 2014

ፍኖተ ነፃነት

የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ቀጠና ኃላፊ አቶ አዕምሮ አወቀ

በደሴ ከተማ የሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ለማስተባበር ወደ ስፍራው የተጓዙት የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ቀጠና ኃላፊ አቶ አዕምሮ አወቀ ድብደባና ዝርፊያ እንደተፈፀመባቸው ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡

ዓርብ መጋቢት 19 ቀን 2006 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡15 ላይ በደሴ ከተማ በተለምዶ ቶታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዕራት በልተው ሲወጡ ታርጋ የሌለውና መስታወቱ ጥቁር በሆነ ኮብራ መኪና አጠገባቸው መጥቶ ሲቆም ከውጪ ሁለት ሰዎች ገፍተው ወደ መኪናው እንዳስገቡአቸው ጨምረው አስረድተዋል፡፡ በመቀጠልም አፍና አፍንጫቸው ላይ ለጊዜው ምንነቱ ያልታወቀ ፈሳሽ ነገር ከነፉባቸው በኋላ መኪናው ተዘግተው ድብደባ ፈጸመውባቸዋል፡፡ እሳቸውም ድብደባውን ሲከላከሉና የመኪናውን መስታወት ለመስበር ሲታገሉ ደብዳቢዎቹ ከኪሳቸው ውስጥ 1735 ብር፣ የነዋሪነት መታወቂያ፣ የፓርቲው የብሔራዊ ምክር ቤት መታወቂያ ወስደው ከመኪናው ገፍትረው እንደጣሏቸው ገልጸውልናል፡፡ –

Previous Story

በ ሱዳን ሀገር ውስጥ በኢትዮጽያዊያኖች ላይ ቤት ለቤት አፈሳ

Next Story

ቴዲ አፍሮ በጊዮን ሆቴል ለዳግማ ትንሣኤ ለሚያቀርበው ኮንሰርት 1.2 ሚሊዮን ብር ተከፈለው

Go toTop