በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በርካታ ተማሪዎች በፀጥታ ኃይሎች ተደበደቡ

March 14, 2022

# ዩኒቨርስቲው ላለፉት 7 ቀናት በውጥረት ላይ ይገኛል!
፣ ህክምና ላይ ይገኛሉ!

ትላንት መጋቢት 4/2014 ዓ.ም 6 ኪሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ “ነፍጠኛ ዳውን ዳውን”በማለት በሚታወቁ ተማሪዎች ባስነሱት ረብሻ በርካታ ተማሪዎች በፀጥታ ኃይሎች ተደብድበው በሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
ትላንት አመሻሹ ላይ “ነፍጠኛ ዳውን ዳውን” የሚሉ ተማሪዎች ላለፉት 7 ቀናት ሲያደርጉ እንደቆዩ፣ የፀጥታ አስከባሪዎች ካምፕ አቅራቢያ ተሰባስበው ሲመካከሩ ከቆዩ በኋላ፣ በተማሪዎች የመኝታ ብሎኮች /ዶርሞች/ እየዞሩ የክፍሎችን በር በመደብደብ፣ “የአማራ ተማሪዎች ውጡ” በማለት ረብሻ በመፍጠራቸው፣ አንዳንዴም ድብደባ በመፈፀማቸው፣ የፀጥታ ኃይሎች ወደ ተማሪውቹ ዶርሞች ተሰማርተው ባገኙት ተማሪዎች ላይ ሁሉ በፈፀሙት ድብደባ ብዙ ጉዳት ደርሷል፡፡
ከአድዋ ክብረ በዓል ክብረ ማግስት ጀምሮ፣ በግቢው ማንነቱ ባልታወቀ ቡድን በተበተነ ወረቀት ላይ “ኦሮሞ ተሰድቧል” በሚል መነሻ፣ በአማራ ተማሪዎች ላይ ድብደባ፣ ስድብና ዛቻ ሲፈፀም መሰንበቱን ምንጮች ተናግረዋል፡፡ በዚህ ሂደት፣ የግቢው ፀጥታ ኃይል ህግ ማስከበር ካለመቻሉም በላይ፣ ድብደባ ከሚፈጽሙ ተማሪዎች ጋር አብሮ ጥቃት እየፈፀመ ስለመሆኑ ለዩኒቨስርቲው አስተዳደር አቤቱታ ቀርቦ እስከመተማመን መደረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በግቢው ውስጥ እየደረሰ ባለው ጥቃት የተፈጠረው ውጥረት እጅግ በመባባሱ፣ የአማራ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ለመውጣት እስከመገደድ የደረሱ ሲሆን፣ የዩኒቨርስቲው አስተዳደር በበኩሉ የመማር ማስተማሩ ሂደት እንዳይቋረጥ ችግሩን በማደባበስ ለመፍታት እየሞከረ ይገኛል፡፡
#መረጃ #ትኩረት

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ


በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጸጥታ ችግር ለመፍጠር የሞክሩ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

***************
(ኢ.ፕ.ድ)
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጸጥታ ችግር ለመፍጠር የሞከሩ ተማሪዎች እና በግቢው ግጭት ለመፍጠር የሞከሩ አካላት ከፀጥታ ሃይሎች ጋር በቅንጅት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና፤ የጸጥታ ሁኔታውን ለማረጋገጥ ከከተማው የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን አስፈላጊው ጥበቃ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በዩኒቨርሲቲው የፀጥታ ችግር ለመፍጠር የሞከሩ ተማሪዎች እና በግቢው ግጭት ለመፍጠር የሞከሩ አካላት ከፀጥታ ሃይሎች ጋር በቅንጅት በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ጠቁመዋል፡፡
አሁን ላይም ዩኒቨርሲቲው መደበኛ የመማር ማስተማር ተግባሩ እንደቀጠለ መግለጻቸውን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ብልጽግና 45 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን በማስመረጥ ጉባኤውን አጠናቀቀ

Next Story

መረጃ ኃይል ነው። ዘ-ሐበሻ ርእስ አንቀጽ

Go toTop