በአሁኑ ሰዓት አማርኛ ተናጋሪው ወገናችን ላይ መለኪያ የሌለው ግፍ እየተፈፀመበት ነው። ይህ ግፍ፤ የአማራውን ወገናችን ለማጥፋት ከሚደረግ ወንጀል ሌላ፤ መገንዘቢያ ቀመር የለውም። የዛሬው እስከመቼ ይኼን ጉዳይ ይመለከታል። በሥልጣን ላይ ያለው ዘውገኛ አምባገነን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፤ አስተዳደሩ በዘውግ ላይ የተመሠረት ስለሆነ፤ አንደኛውን አስበልጦ ሌላውን አሳንሶ መመልከቱና በዚያ ፈለጥ ማስተዳደሩ ምንነቱ ነው። አልፎ ተርፎ ግን፤ አንድን ወገን ለይቶ፤ በዚህ ወገን ላይ የተለዬና ጭካኔ የተሞላበት በደል መፈፀም፤ መሠረታዊ ተልዕኮውን እንድንመረምር ያስገድደናል።
- March 2012, No. 101
- March 2012, No. 102