Hiber Radio: የረዳት አብራሪው መጪው ዕጣና ከዚህ በፊት በአውሮፕላን ተደብቆ ቤልጂየም የገባው ኢትዮጵያዊ እንዴት በስርዓቱ ማጭበርበር ተላልፎ ተሰጠ?

February 25, 2014

የህብር ሬዲዮ የካቲት 16 ቀን 2006 ፕሮግራም

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
<...ረዳት አብራሪ ሀይለመድሕን አበራ ለኢትዮጵአውያን ጀግናችን እንደ የኔሰው ገብሬ ነው...ስዊዘርላንድ ኤምባሲ ፊት ለፊት በዲሲ የምናደርገው ሰልፍ አገሪቱ ለህወሃት ጨካኝ አገዛዝ አሳልፋ እንዳትሰጠው ለመጠየቅ ነው ...>

አክቲቪስት መስፍን አስፋው ከዋሽንግተኑ የድጋፍ ሰልፍ አስተባባሪዎች አንዱ ለህብር ከሰጠው ቃለ መጠይቅ

<<...የአማራ ሕዝብን ያዋረደው ብአዴን ወኪል ነኝ ብሎ እንዳያወራ ! አቶ አለምነው ለፍርድ እንዲቀርብ ይቅርታም እንዲጠይቅ...>> የመኢአድ ሊቀመንበር አቶ አበባው መሐሪ በባህር ዳር ለተቃውሞ ለወጣው ሕዝብ ካደረጉት ንግግር

<<... የአማራን ሕዝብ ያንቋሸሸውና ያዋረደው አቶ አለምነው ለፍርድ ካልቀረበና ይቅርታ ካልጠየቀ ተቀውሞ ሰልፉ ይደገማል...>>

ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር በባህር ዳር ለተሰበሰበው ሕዝብ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ(ዘገባውን ያዳምጡ)

የረዳት አብራሪው መጪው ዕጣና ከዚህ በፊት በአውሮፕላን ተደብቆ ቤልጂየም የገባው ኢትዮጵያዊ እንዴት በስርዓቱ ማጭበርበር ተላልፎ ተሰጠ?( ወቅታዊ ዘገባ ይዘናል)

የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር እና የህወሃት በሸር የተወጠነ ድርድር ሲቃኝ(ክፍል ሁለት)

ሌሎችም ዝግጅቶች

ዜናዎቻችን

– ስዊዘርላንድ ከአገሯ ረዳት አብራሪዎን አሳልፋ እንዳትሰጥ እየተጠየቀ ነው

– ነገ በዲሲና በፍራንክፈርት አርብ በስዊዘርላን የአገሪቱን መንግስት ለመጠየቅ ሰልፍ ይደረጋል

– ኦብነግ ሰሞኑን ሰባት የኢትዮጵያውን አገዛዝ የጸጥታ ሰዎችን ገደልኩ አለ

– በባህር ዳር ነዋሪዎች ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል ሲሉ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

– የአማራን ብሔር የተሳደቡ የክልሉ ም/ል ፕሬዝዳንት ለፍርድ እንዲቀርቡ ተጠየቀ

* ለተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ገበሬዎች ታስረዋል

– ሱዳን ውስጥ በወረበሎች የተደፈረች ኢትዮጵያዊት ትፋተኛ ተባለች

– በቤይሩት ቦንብ ፍንዳታ ኢትዮጵያዊቷ ሕይወቷ አለፈ

– በሚኒሶታ የሚኖሩ የኦሮሞ ማህበረሰብ ዘርፈ ብዙ የሆነ ድህረ ገጽ ሊከፍቱ ነው

በቬጋስ የየካቲት 12 የሰማዕታት ቀን ተከበረ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Previous Story

Over 1 million babies die on day of birth yearly

Next Story

የኢትዮጵያ ሴቶች ጉዳይ ሚ/ር ዘነቡ ታደሰ ዩጋንዳ የጸረ ጌይ ሕግ ማውጣቷን ተቹ

Go toTop