የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልት
ጉዳዩ የሰብዓዊመብት ጥሰትን ይመለከታል
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ሕገመንግሥት አንቀጽ 55 የሕዝብ ተወካዮች ምከር ቤት ሥልጣንና ተግባር በተመለከተ በተራ ቁጥር 16 ፦
በማንኛውም ክልል ሰብዓዊመብቶች ሲጣሱ ክልሉ ዲርጊቱን ማቆም ሳይችል ሲቀር ፣ በራሱ አነሳሽነትና ያለ ክልሉ ፈቃድ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ለፌደረሽኑ ምክር ቤትና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ጥያቄ ያቀርባል፤ በተደረሰበት ውሳኔ መሰረት ለክልሉ ምክር ቤት መመሪያ ይሰጣል ።
በተራ ቁጥር 17 ፦
ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚንስትሩን እና ሌሎች የፌደራሉ መንግሥት ባለስልጣናትን ለጥያቄ የመጥራትና የሕግ አስፈጻሚውን አካል አሠራር የመመርመር ሥልጣን አለው ይላል ።
ክቡራን የምክር ቤቱ አባላት ለውጥ መጣ ከተባለ ጊዜ አንስቶ በአገራችን በአጠቃላይ ሰላም ከሰማይ እርቋል ፤ በኦሮሚ ክልል በተለይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፣ የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ዘመቻ በክልሉ መንግሥት አስተዳደራዊ መዋቅር ድጋፍና ትብብር እይተካሄድ ለመሆኑ ከጥቃቱ ሰለባዎች አፍ እየሰማንና በአይናችን እያየነው ነው ። አማራ በሰሜን ከትግራይ ወራሪ ኃይል የህልውና ተጋድሎ በማደረግ ለይ ሲሆን በደቡብ በኦሮሚያ ክልል እለት ተእልት እየተጨፈጨፈና ሀብት ንብረቱ እየወደመበት ለክልሉ መንግሥት በተደጋጋሚ አቤቱታ ቢያቀርቡም ሊሰሟቸው ይቅርና ለአቤቱታ የመጡትን የክልሉ መንግሥት ታጣቂዎች ደብድበውና አዋርደው ይመልሷቸዋል ። ይህ የሚያመላክተን ድርጊቱ በክልሉ መንግሥት ቡራኬና ተሳትፎ መሆኑን ነው። ስለሆነም የተከበረው ምክር ቤት በሕገመንግሥቱ የተሰጠውን መበት ተጠቅሞ ፦
- ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ከፌዴረሽን ምክር ቤት ጋራ ስብሰባ በመድረግ በክልሉ የሚካሄደውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲቆምና ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ መመሪያ እንዲሰጥ ፤
- ምክር ቤቱ በሕገ መንግሥቱ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድንና የክልሉን ምክትል ፕሬዚደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጠርተው እንዲያነጋግሩና ጉዳዩን እንዲመረምሩ በትህትና እንጠይቃለን (እጠይቃለሁ)፤
- ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚንስቲሩ ዶክተር አብይ አህመድ ከሕዝብ እውቅና ውጭ በማን አለብኚነት በፓርላማ በአሸባሪነት ከተፈረጁ ኃይሎች ጋር የሚያካህዱትን ማንኛውንም ውይይት ፣ ስምምነትና እርምጃ ህገ ወጥ በመሆኑ በተሰጣችሁ ሕዝባዊ አደራና ሕገመንግሥታዊ መብት በመጠቀም እንድትመረምሩና ውጤቱን ለወከላችሁ ሕዝብ ይፋ እንዲታደርጉ እንጠይቃለን ።
ይህ ሳይሆን ቀርቶ የተጀመረው የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ወንጀል ቀጥሎ በሀገርና በሕዝብ ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም ጥፋት ምክር ቤቱ በወቅቱ ኃላፊነቱን ባለ መወጣቱ ተጠያቂ ይሆናል ።
ኢትዮጵያ አንድነቷ ተጠብቆ ለዘላለም ትኑር
ንጉሤ አሊ