የኤርሚያስና የጃክ ማ ሽርክና አደገኝነትን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማብራራት ልሞክር – ካሳ አንበሳው

January 22, 2022

ሰዋቹ ተሻርከናል የሚሉት አንድን ጫፋ ከሌላኛው ጫፍ የሚያገናኝ የበይነ-መረብ ኤሌክትሮኒክስ ገበያ (end to end e-commerce) ምስረታ ላይ ነው፣ ይህ ማለት ከአምራቹ (ከነጋዴው) ወለል አንስተው ገዥው በር ላይ ያደርሳሉ፣ የክፍያ፣ የመጋዘንና የትራንስፓርት (የባህር፣ አየርና ምድር) ጉዳዬችን እራሳቸው ይጨርሳሉ፣ ይህን አንድ ብለህ ያዝልኝ፣

የሁለቱ ሻርኮሽ ሽርክና የኢትዮጵያን ገበያ ከሌላው አለም ገበያ (በተለይ ከቻይና ጋር) virtually ይቀላቅለዋል፣ ይህን ሁለት ብለህ ያዝና የሀገራችን ድርጅቶች አቅምና የተወዳዳሪነት ደረጃን እያሰላሰልክ ቆይ፣ ንግዱ one way እንደሚሆን ይገለጥልሀል፣

ሻርኮቹ ‘ተሻረክንበት’ የሚሉት አምራችን ከሸማች ያገናኛል የሚባለው የበይነ-መረብ ገበያ (end to end e-commerce) የተለመደው “traditional” ገበያ ውስጥ ያሉትን እንቅፋቶች (barriers) “የት ነበሩ?” እስክንል ድረስ ሙልጭ አድርጎ ያስወግዳቸዋል፣ acid wash ያደርጋቸዋል፣ ይህ ማለት አዲስ አበባ ቁጭ ብለህ ከቻይና አምራች/ነጋዴ መግዛት የሁለት/ሶስት ክሊኮች ጉዳይ ብቻ ይሆናል፣

[በነገራችን ላይ ሀገራት የራሳቸውን አምራቾች ከቻይና ጥቃት የሚከላከሉት ሆን ብለው እንቅፋት (trade barriers) በማብዛትና ከቻይና አምራች/ነጋዴ መግዛት አስቸጋሪና ውድ በማድረግ ነው፣ አንዳንድ ምርቶችን ከነአካቴው ያገዱ (ban ያደረጉም) አሉ]

“ሻርኩ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዋቻችንን ይሰለቅጥብናል፣ ይህን-ወይም-ያን ኢንደስትሪ ይጎዳዋል” እያልን መተንተን ለኛ ቅንጦት ነው፣ ለዛ ቅንጦት ያልደረስን መናጢ ድሆች ነን፣ አሉን የምንላቸውን ጥቂት ፋሪካዋችን አጎዋ አስበርግጓቸዋል፣ ኤርሚያስ እስከወዲያኛው ያሰናብታቸዋል፣ እኔ እየሰጋሁ ያለሁት ለሸማኔው ጭምር ነው፣

ቻይና ተሰርቶ የሚመጣ የሀገር ባህል ልብስ እንዳለ በቅርብ ነው ያወቅኩት፣ የሻርኮቹ ሽርክና ነጠላ ቋጭተህ እንኳን እንዳትበላ ነው የሚያደርግህ፣ ሮቦት እዛው ቻይና ውስጥ ይቋጨዋል፣ ሰፌድ አይቀርም፣

ሽርክናው መሬት ላይ ሲወርድ መቶ ወይም ሁለት መቶ ሰራተኞችን ሊቀርጥር ይችላል (ቆየት ሲል በሮቦት መተካታቸው አይቀርም)፣ ትንንሽ አምራች ድርጅቶችንና ቸርቻሪዋች (retail shops) ሲሰለቀጡ ለመታዘብ ግን አምስት ዓመት መጠበቅ ይኖርብሀል፣ በመጀመሪያው አራት አምስት አመት ሸማችና ኤርሚያስ ደስተኞች ናቸው፣ ከአምስት አመት በኃላ ኤርሚያስና ሸሪኩ ብቻ ናቸው ደስተኞች፣

“ህምምም ሲጀመር ሸማቹ የውጭ ምንዛሬ አያገኝም፣ ስለሆነም ጉዳዩ የሚያሳስብ አይደለም የሚል አይጠፋም” እንዲህ ያለ አስተሳሰብ/ግምት ኤርሚያስን ካለማወቅ የሚመነጭ ነው፣ ኤርሚያስ ብልጣ ብልጥነትን ከአርቆ አሳቢነት ጋር የተካነ ኮርማ ነው፣ ያሰላል፣ ያሰላስላል፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የውጭ ምንዛሬ ጥቁር ገበያ (black market) ትልቅ እንደሆነ ኤርሚያስ አያጣውም፣ እድሉን ካገኝ ከዚህ በላይ ሊሰፋና ሊጠልቅ እንደሚችል ይገባዋል፣ የኤርሚዬስ ታርጌት ያ ነው፣ ሽርክናው እውነት ሁኖ ስራ ላይ ከዋለ በጥቁር ገበያ ውስጥ የሚሽከረከረው የ$፣ £ ወይም € ኖት ሳይሆን የውጭ ሀገር ባንኮች debit/credit card ነው፣

ካሳ አንበሳው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ለጥምቀት በዓል የወጡ ምዕመናን ቡራዩ ላይ ሁለት ሰዎች ተገደሉ

Next Story

የ ፴ ዓመት መከራ – ማላጂ

Go toTop