“የአማራ ኢሊቶች..”? – ጌታችው አበራ

December 12, 2021

የወያኔ ሮሮ፣
የጅል እንጉርጉሮ፣
ሲዘመር ሰምቼ፣
ጆሮዬን አቅንቼ፣
ሳዳምጥ በብርቱ፣
ነበር ለካስ ከንቱ!

“ሂሳብ ማወራረድ..
ከአማራ ኢሊቶች”፣
ይል ነበረ ግጥሙ..
የጭካኔው አዝማች፤
ያረመኔ ተግባር ..
ቢሆንም ድርጊቱ፣
መስሎኝ የነበረው..
ሰው ነበር “ኢሊቱ”፤

ለካስ በወያኔ፣
በደደቢት ቅኔ፤
ጥማድ በሬዎቹ፣
ላሞች ጥገቶቹ፣
በጎች ፍየሎቹ…
ነበሩ “ኢሊቶች”..
ያማራ ሃብቶቹ።

እንሰሳት ገዳዩ፣
ቡሃቃ አማሳዩ፣
ሆስፒታል ነቃዩ፣
ሬሳ አቃጣዩ…፣
አረመኔ ጨካኝ..
ቦቅቧቃ ማፊያ፣
ወያኔ! ወያኔ!..
የአገር ማፈሪያ!

ጌታችው አበራ
ታህሣስ 2014 ዓ/ም
(አኤፕሪል 2021)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ጉዞ ወደ መቀሌ | አክሱም ፅዮንን ተሳልመን እንመለሳለን | በደሴ የተገኙ ፋኖዎች ተጋድሎ | Ethio 251

Next Story

ሸዋ ግንባር ጀግናው ልዩኃይል ጀግናው መከላከያችን ጀግናው የፋኖ አናብስቶች ጠላትን እየየ ያሰኙበት የሸዋ ግንባር በጥቂቱ ክብር ለሁላችሁም

Go toTop