በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በግለሰባዊ ማንነቱ የታሰረ የለም

November 12, 2021

እየተካሄደ ያለውን የህልውና ዘመቻ ባጠረ ጊዜ ለመቋጨት በተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በግለሰባዊ ማንነቱ የታሰረ አንድም አካል አለመኖሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ።

አምባሳደር ሬድዋን ከአልጀዚራ ሆርን ኦፍ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ባልተፈቀደ ድርጊት የተሰማራ ማንኛውም ግለሰብ ተጠያቂ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።

ፖሊስ በሚደርሱት መረጃዎች መሰረት ምርመራ እንደሚያደርግ አመልክተው፤ የትኛውም ግለሰብ በብሄሩና በሌሎች ግለሰባዊ ምክንያቶች አልታሰረም ሲሉ አስታውቀዋል።

በፖሊስ በሚያካሂደው የመረጃ ማጣራት ግለሰቦች ካልተፈቀደ ድርጊት ነጻ መሆናቸው ተረጋግጦ ነጻ እንደሚለቀቁ ነው የገለጹት።

ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት የህልውና ዘመቻና የህግ ማስከበር ተግባር ላይ እያንዳንዱ ነገር ቁጥጥር እንደሚደረግበትም ጠቁመዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ሰራተኞች ታስረዋል በሚል በሚነሳው ጉዳይ ላይ በሰጡት ማብራሪያ “ግለሰቦቹ የታሰሩት የተመድ ሰራተኞች በመሆናቸው ሳይሆን የአገሪቱን ህግ ተላልፈው በመገኘታቸው ነው” ብለዋል።

የእርዳታ እህል ጭነው የገቡ ከ800 በላይ ተሽከርካሪዎች ለአሸባሪው ህወሃት መንቀሳቀሻና ለሽብር ተግባሩ ማስፈጸሚያነት እየዋሉ መሆኑን ገልጸው፤ “መንግስት ላይ ስሞታ የሚያቀርቡ አካላት ይህንን በተመለከተ ግን አንድም ጥያቄ ሲያነሱ አይታይም” ሲሉ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት ወደ ትግራይ 300 እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች እየተጓጓዙ መሆኑን አመልክተው፤ የሰብአዊ ድጋፍ በሚደረግባቸው አካባቢዎች አሸባሪው ህወሃት የተኩስ አቁም ስምምነቱን በመጣስ ወደ ጦርነት መግባቱንና መንግስትም ዜጎችን ለመጠበቅ እርምጃ መውሰዱን አስታውቀዋል።

ድጋፍ አልተደረገም’ ብለው የሚወቅሱ አካላት ድጋፍ በሚደረግባቸው አካባቢዎች ተኩስ አቁሙን ጥሶ ጦርነት የከፈተው አሸባሪው ህወሃት ሆኖ ሳለ ለምን መሸፋፈን መረጡ ሲሉ ጠይቀዋል።

አንዳንድ የተመድ ሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ አካላትም የተፈቀደላቸውን ሰብአዊ ተግባራት ከማከናውን ይልቅ የአሸባሪው ህወሃት ወራሪ ሃይል በኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርሰውን ግፍ በመሸፋፈን ተጠምደዋል ሲሉ አስታውቀዋል።

አዲስ አበባ ተከባለች መንግስት ስልጣኑን ሊለቅ ነው’ በማለት እንደ ሲኤንኤን፣ ሮይተርስና ቢቢሲ ባሉ በአለም ዓቀፍ ሚዲያዎች የሚሰራጨው መረጃ በሬ ወለደ ከመሆኑ በላይ ድብቅ አጀንዳ የያዘ ነውም ሲሉ ገልጸዋል።

_ አካባቢህን ጠብቅ፣

_ ወደ ግንባር ዝመት፣

_ መከላከያን ደግፍ።

ህዳር 03 ቀን 2014 (ኢዜአ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የአሜሪካና ምዕራባውያን ጫናና መፈንቅለ መንግሥት በግርማዊነታቸው መንግሥት ላይ!! – መስፍን ማሞ ተሰማ

Next Story

ደም ተቀብቶ ዝንብ መፍራት አይሆንም ፤አያዛልቅም ፡፡

Go toTop