ሽንፈት ታሪካችን አይደለም። ለኢትዮያውን ወደ ሰላም መመለስ ይፈልጋሉ። ይህንንም ግብ አድርገን እንሠራለን።
ኢትዮጵያ ጥንታዊት ብትሆንም ባለፉት 30 አመታት ወንድማማችነትን የሚያላላ ብዙ ሥራ ተሰርቷል። አሁን የምንሠራው ሥራም ኢትዮጵያን አለት ላይ የመገንባት ታላቅ የሀገር ግንባታ ሥራ ነው። ኢትዮጵያ ፈተናዎችን ሁሉ አልፋ በፅናት ቀና ብላ የድል ታሪኳን ለሌሎችም የምታስተምር እንድትሆን በርካታ መስዋዕትነት እየከፈልን እንገኛለን።” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
=====================
አንድነታችንን ጠብቀን ኢትዮጵያ በፈተናዎች የማትወድቅ ጠንካራ ሀገር መሆኗን በተግባር እናሳያለን
አዲስ አበባ፤ ህዳር 2/2014 (ኢዜአ) አንድነታችንን ጠብቀን ኢትዮጵያ በፈተናዎች የማትወድቅ ጠንካራ ሀገር መሆኗን በተግባር እናሳያለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በሚዘጋጀው “አዲስ ወግ” በተሰኘው የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው።
የውይይት መድረኩ “የህልውና ጥሪ እና ሀገርን የማዳን ርብርብ” በሚል ርእስ የተካሄደ ሲሆን፤ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት በአሸባሪው ህወሓት የተከፈተውን ጦርነት ለመረዳት ወደ ኋላ መለስ ብሎ ነገሮችን መመልከት እንደሚገባ አንስተው፤ አሸባሪ ቡድኑ ኢትዮጵያን የማፍረስ ውጥኑን የሚጀምረው ከምስረታው እንደሆነ ተናግረዋል።
የቅራኔው መሰረት የአሸባሪው ህወሃት ኢትዮጵያውያንን በማባላት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ካለው ጽኑ ፍላጎት እንደሚመነጭ ነው የገለጹት፡፡
በተጨማሪ በመዋቅር የታገዘ ዘረፋ መሆኑን ጠቅሰው፤ ዘረፋውም ንብረትን፣ ማንነትንና መሬትን የሚያካትት መሆኑን አብራርተዋል፡፡
አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ጦርነት የማጭበርበር ጦርነት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በተደራጀ መልኩ የሀሰት መረጃዎች እየተነዙ መሆኑን ገልጸዋል።
አሸባሪ ቡድኑ ቢዋሽ የሚጠይቀው አካልም ሆነ እንዳይዋሽ የሚከለክለው የሞራል ቁመና የሌለው መሆኑን ገልጸው፤ በዚህም እንዳሻው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እያሰረጨ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
“በመሆኑም በአሁኑ ወቅት መሠረታዊ ጦርነት ጥይቱ ሳይሆን የሀሰት ወሬው ነው” ብለዋል፡፡
አሸባሪው ህወሃት በትጥቅ ትግል ወቅት ሲጠቀምበት የነበረውን የአረጀ ስልት አሁንም ለመድገም እየሞከረ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም ሊሳካ የማይችል ከንቱ ልፋት ነው ብለዋል፡፡
አሸባሪ ቡድኑ ዛሬም ስትራቴጂ ሳይቀይር የተለመደውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እየነዛ መሆኑን አክለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በገጠሟት ፈተናዎች እየተሰራችና እያሸነፈች ወደ ከፍታ እንደምትወጣ ያረጋገጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ በፈተናዎች የማትወድቅ ጠንካራ ሀገር መሆኗን ለቅርብም ለእሩቅም ጠላት እናረጋግጣለን ብለዋል።
ዛሬ ላይ ኃያል የምንላቸው ሀገሮች በታሪክ አጋጣሚ ኢትዮጵያን አሁን የገጠሟትን መሳይ ፈተናዎች አልፈው ለዚህ መብቃታቸውን ለአብነት አንስተዋል።
“አትዮጵያና ሽንፈት ፈጽመው አይተዋወቁም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በመሆኑም ኢትዮጵያም አሁን የገጠሟትን ፈተናዎች በድል ተሻግራ በአሸናፊነት የሚነሳ ታሪክ ትጽፋለች ብለዋል።
በመሆኑም ኢትዮጵያውያን በፈተናዎች ሳይንበረከኩ ኢትዮጵያን እና አሸናፊነትን ዳግም ማስተሳሰር አለባቸው ነው ያሉት።
-አካባቢህን ጠብቅ
-ወደ ግንባር ዝመት
-መከላከያን ደግፍ
መረጃዎቻችንን ለማግኘት