ብርጋዴር ጄኔራል ኃይሉ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት አስተያየት የጥቂት ሰዎች ስብስብ የብዙኃኑን ፍላጎት በመጫን ያውም አገር በማፍረስ ወደ ሥልጣን የሚመለስበት ሁኔታ ዳግም በኢትዮጵያ ምድር የማይመለስና የተዘጋ አጀንዳ ነው፡፡
አሸባሪው ህወሓት ባወጀው ጦርነት ከጅምሩ ተሸናፊ ከሚያደርጉት አፍራሽ አስተሳሰቦቹ ውስጥ “ ሲኦልም ቢሆን ገብቼ ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ” የሚለው አንዱ ሲሆን ኢትዮጵያ ስትፈርስ ደግሞ ቆሞ የሚመለከት ዜጋ ስለሌለ የቡድኑ ሽንፈት መጀመሪያውኑ ከንግግሩ ጋር አብሮ የታወጀ መሆኑን ብርጋዴር ጄኔራል ኃይሉ ጎንፋ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ብሎ ከጅምሩ ወደ ትግል መግባት የሽንፈት ሁሉ መጀመሪያ ነው ያሉት ብርጋዴር ጄኔራሉ የአሸባሪው ህወሓት ጭካኔ የተሞላበት አደገኛ አካሄድ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ቡድኑ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በኃይል በማንበርከክ የትናንቱን አፈናና ግድያን ዳግም ለመጫን የሚያደርገው መፍጨርጨር በየትኛውም ስሌት የማይሳካና የወደቀ የፖለቲካ አመለካከት ውጤት ነው ብለዋል፡፡
(ኢ ፕ ድ)