ጆሮ ያለው ይስማ፣ ልብ ያለው ይነሳ ፣አቅም ያለው ይዝመት (ከእውነቱ)

August 10, 2021

ትህነግ በህዝቡ እልህ አስጨራሽና መራራ ትግል ከአገሪቱ ወሳኝ የፖለቲካ ወንበር ከተወገደ በኋላ የመሪነት ፖለቲካው በኦሮሙማ በመተካቱ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ከድጡ ወደማጡ ሆኗል፡፡ በአሁኑ ሰአት የኢትዮጵያ ጦር በኦሮሙማ የክህደት ሴራ እየታመሰና ስትራቴጅክ ማፈግፈግ በሚል ሽፋን ገዥ መሬቶችንና ከባባድ መሳሪያወችንም ጭምር ለትህነግ ለቀህ ውጣ በሚል ትእዛዝ ከየጦር ግንባሮቹ እየለቀቀ ነው፡፡ይህ የኦሮሙማ ተንኮል የአማራው ህዝብ እንዲያልቅና ለም የአማራ መሬቶችም ለመደራደሪያነት በትህነግ ቁጥጥር ስር እንዲወድቁ ታቅዶ እየተሰራበት ነው፡፡

የድርድሩና የማፈግፈጉ ቁልፍ ምስጢሩ ምንድን ነው? ምን ግቦችንስ ታሳቢ ያደረገ ነው ብለን ስንጠይቅ የሚከተለውን መልስ እናገኛለን፡፡ ድርድሩ የሚካሄደው በምእራባዊያን ድብቅ አደራዳሪነት በትህነግና በኦሮሙማው ቁንጮ አብይ አህመድ መካከል የሚደረግ ቁማር ነው፡፡ የድርድሩ ጭብጥም ወያኔ የኔ ናቸው የሚላቸውን የወልቃይትና ራያ ለም የአማራ መሬቶችን ከአማራ ክልል በቀጥተኛ መልኩ ለማስመለስ አብይን ስላስቸገረው በተዘዋዋሪ መንገድ እነዚህ መሬቶች በትህነግ ጦር እንዲያዙ ተደርጎ ለመደራደሪያነት እንድቀርቡ ለማድረግ ነው፡፡ ከዚያስ?

ከዚያማ ትህነግ በድርድሩ ሂደት ከአማራ ክልል የምወጣው ተይዘውብኝ ነበር የሚላቸውን የራያና የወልቃይት መሬቶች የእርሱ እንደሆኑ እውቅና አግኝተውለት ቦታወቹ እንደቀድሞው በትግራይ ስር ሲሆኑ ብቻ ነው ብሎ ለድርድሩ ይቀርባል፡፡ አብይ አህመድም በበኩሉ ፌደራል መንግስቱ የሚደራደረው[“ትህነግን አሸባሪ ነው”ማለቱንና የበነነ ዱቄት ነው ማለቱን ረስቶ??] ትህነግ እስከ ወልድያና ላሊበላ ድረስ ዘልቆ ያያዛቸውን የአማራ መሬቶች በህገ መንግስቱ መሰረት በፊት እንደነበረው ከአማራ ክልል ለቅቆ ሲወጣ ብቻ ነው ብሎ ለድርድሩ ይቀርባል፡፤ ይህ የመደራደሪያ ቁማር ከሁለቱም ተደራዳሪወች በሁለቱም የቢለዋ ስለቶች አማራን ያረደና አማራን ያስበላ ቁማር ነው፡ ፤፣ መሬቶቹንም ያስነጠቀና ከእንግዲህ ወዲያ ኦሮሙማ በንግስናው እስከቀጠለ ድረስ አማራው አንገቱን ቀጥ አድርጎ እንዳይሄድ ያደረገ አንገት አስደፊ ቁማር ነው፡፡[[ እዚህ ላይ የአማራ መሪወች ነን ባዮችን አስጠቂነትና የታሪክ አተላነት ራሱ ታሪክ በጥቁር መዝገብ ይዞት ይኖራል፡፡የፋኖ ወጣቶች መርሳ ላይ የማረኩትን የጠላት መሳሪያን መንጠቅንና የወልዲያ ከተማን በመድፍ የመደብደብ የድረሱልን ጥሪንም አይዘነጉትም]]

በድርድር ውጠቱም ትህነግ ለም የራያና የወልቃይት የአማራ መሬቶችን ወደራሱ በማድረግ ይህንኑ በእውቅና አስከብሮ በአሸናፊነት በመውጣት የትግራይ ህዝብን በሪፍረንደም አሳቦ ታላቋን ትግራይን በነጻ አገርነት እንዲመሰርት ሲያስችለው ለአብይ አህመድ ደግሞ በኮሳሳው አማራ የበታችነት የምትኖር፣ ኦሮሞ የነገሳበት፣ ቀሪዋን ኢትዮጵያ እየገዛ እንዲኖር ያስችለዋል፡፤ ቁማሩ እዚህ ላይ ያበቃል ፤ ይህ አይነቱ የፖለቲካ ቁማር ምእራባዊያን በብዙ አገራት በሰፊው የተካኑበት ትህነግም በሙሉ አቅሙና በእድሜው ልክ ጥፍሩን ነቅሎ ያደገበት የሸፍጥና የተንኮል ፖለቲካ ውጤት ነው፡፡

አብይ አህመድ ሆይ፦አሁን 11ኛው ደቂቃ ላይ ብንገኝም፡፤በዜግነታችን የመጨረሻ ምክራችንን ስማን፡፡ የለበስከውን የኦሮሙማ ካባ አሽቀንጥረህ ጣልና የኢትዮጵያዊነትን ካባ በምሉእ ተላበስ፡፤ እጅግ የዘገየህ ቢሆንም ለእስካሁኑ ወንጀሎችህ ቢያንስ ንስሀ ግባና ከእንግዲህ በኋላ በአገርና በህዝብ ላይ የሚሰራውን ደባ ሁሉ ሙሉ በሙሉ አስቁም፡፡እኛ በቃ ብለናል፡፡አንተም ይህንን ካደረግህ ደጋፊህ መስለው ከተደበቁ የውስጥም የውጭም ጠላቶችህ ትድናለህ፡፤ህዝቡም እቅፎና ደግፎ ይይዝሀል፡፤ለማንም አሳልፎ አይሰጥህም፡፤ ይህንን ካላደረግህ ግን ትጠፋለህ፡፡አማራው በበኩሉ በትህነግ፣ በኦሮሙማና በራሱ ሆዳሞች ጭምር የተሰራበትን ግፍ፣ ተንኮል፣ ሴራና እልቂት ከባድ መስዋእትነትን በመክፈል ጠላቶቹን ድል መትቶ ራሱን ነጻ ያወጣል፡፡ለዚህ ሳይንሳዊና ነባራዊ ሀቅ እውነት መሆን አሁን ላይ በአማራው ውስጥ ሶስት ምሰሶወች (ሶስት ወሳኝ ማሳያወች) ተሟልተው ይገኛሉ ፡፤እነርሱም 1ኛ) ታሪክና ፍርድ የሚያረጋግጠው አማራው ጋር ያለው ህያው እውነት 2ኛ) በአማራው ላይ ለ30 አመታት የተሰራበት ጽዋው ሞልቶ የፈሰሰው ግፍና መከራ

3ኛ) የራሱ የአማራው የአልገዛም ባይነት፣ የነፍጠኛነትና የጀግንነት ውሎወቹ በተጋድሎ የተመዘገቡና የተረጋገጡ ታሪኩ ናቸው፡፡ ለአገሪቱ አጠቃላይ ውድቀትና አሁን ላይ እዚህ ቅርቃር ውስጥ ገብተን ለመገኘታችን ዋናው መንስኤ የትህነግ የ27 አመታት መርዘኛፖለቲካና በዘር ላይ የተመሰረተው ህገ መንግስት ነው፡  ይህ ሀቅ እንዳለ ሆኖ አንተ ስልጣን እንደያዝክና ያኔውኑ ህዝቡ እንዲያ እንደደገፈህ መውሰድ የነበረበህን እርምጃወች ባለመውሰድህ ከዚያም ቀጥሎ በችሎታ ማነስም ይሁን በኦሮሙማው ካባህ እጅግ አስፈላጊ የነበሩ የማስተካከያ እርምጃወችን ሳትወስድ በመቅረትህ በአንተ አመራር ጊዜ ውስጥ ለተፈጠሩት ወንጀሎች ሁሉ ተጠያቂ ነህ፡፡ እኛን እስካሁን የሚሰማን ስሜት የሚከተለው ነው፡፤ እርሱም አንተ ራስህ የኦሮሙማው ካባ በልጦብህ አገሪቱን በኦሮሞ ቅርጽና ይዘት ለመግዛት በመሻትህ አገሪቱንና ህዝቧን እዚህ መቀመቅ ውስጥ እንደከተትካቸው ነው፡፡

አሁንም እንደ ብዙሀኑ ኢትዮጵያዊያን እምነት ከሆነ የአቋምና የአሰላለፍ ለውጥ አድርገህና በኢትዮጵያዊነት አምነህ ለሚተገበር እርምጃ አሁኑኑ እስካልተነሳህ ድረስ አንተ ከእንግዲህ አማራን ብሎም ኢትዮጵያን ትታደጋለህ የሚል ቅንጣት እምነት የለንም፡፡ እንድናምንህ ብቻ ሳይሆን አንተም መሪነትህ እንዲሰምርልህ፣አገርም እንድትድን በዜግነታችን የሚከተሉትን እጅግ አስፈላጊ የመዳኛ እርምጃወችን በአስቸኳይ እንዲትወስድ እንመክርሀለን፡፡1ኛ) ከሸፍጥ ድርድሩ ውጣ 2ኛ) የተናጠል ተኩስ አቁም የምትለውን ቀልድ አቁምና ጦሩን በሙሉ ቁመናው ወደ ውጊያው እንድገባ አድርግ፡፤3ኛ) የትህነግ ነቀርሳወችን ከስሩ ንቀልና ጣል፡፤

4ኛ) ለዚህ ጨምላቃ ዉጊያ እንኳን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የአማራ ፋኖና ልዩ ሀይል በቂ መሳሪያና ሀቀኛ የራሱ አመራር ካገኘ ማንንም ሳይፈልግ ትህነግን ብቻውን ድባቅ ይመታታል 5ኛ) በዚህ ድል ማግስት ወዲያዉኑ አሁን ያለውን የማይሰራ ህገመንግስት አግደህ ለመላው አገሪቱ የእውነተኛ ፌደራል ስርአት የሚስማማ፣ አንዲነትንና ሉአላዊነትን የሚያረጋግጥ ህገመንግስት በቦታው አሳውጅና ተካ፡፡ይህንን በማድረግህም በጥጋበኞችና በውጭ ባንዳ የትህነግ ቅጥረኞች የሚረግፈውን የትግራይ ወጣት ድረስለት፡፡በችጋር የሚቆራመደውንም የትግራይ ህዝብ እንደዚሁ ድረስለት፡፤ በመጨረሻም ከላይ ከ1 እስከ 5 የተጠቀሱትን እርምጃወች በቶሎ ተግባር ላይ ከዋልክ ታላቋ አገራችን ኢትዮጵያ በሀቀኛ ልጆቿ መስዋእትነት ነጻነቷን ጠብቃ፣ ታፍራና ተከብራ ለዘለአለም ትኖራለች፡፡ለዚሁ ስኬት ጆሮ ያለው ይስማ ልብ ያለው ይነሳ አቅም ያለው በየፈርጁ ይዝመት፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

ወልዲያ እንዴት ዋለች??? ሕዝቡን የሚያሸብሩ የመከላከያ አባላት!! | weldiya | endf | tplf
Previous Story

ወልዲያ እንዴት ዋለች??? ሕዝቡን የሚያሸብሩ የመከላከያ አባላት!! | Weldiya | ENDF | TPLF

gizachew
Next Story

የትግሉ ዓላማ አሸባሪውን ሙሉ በሙሉ መደምሰስና ተላላኪዎቹንም የኢትዮጵያ ስጋት እንዳይሆኑ ማድረግ መሆኑ ተገለጸ

Go toTop