ከአንድ ወር በፊት ከቤታቸው በሌሊት ተወስደውና አድራሻቸው ጠፍቶ የቆዬው ጋዜጠኛ ታዲዮስ ታንቱ በአሁኑ ሰዓት ገላን ከተማ ታስረው ተገኙ

August 5, 2021

እጅግ ተጎሳቁለዋል!!!

tadewes tantu
tadewes tantu

 

ከአንድ ወር በፊት ከቤታቸው በሌሊት ተወስደውና አድራሻቸው ጠፍቶ የቆዬው ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ በአሁኑ ሰዓት ገላን ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ታስረው የሚገኙ ሲሆን እስካሁኗ ስዓት ድረስ ፍርድ ቤት አልቀረቡም። ከተያዙበት ዕለት ጀምረው ወደ አዋሽ መልካ ተወስደው ለ22 ቀናት በጨለማ ቤት ታሰረው በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ምግብ እየቀረበላቸው ከቆዩ በኋላ አሁን ወደሚገኙበት ጣቢያ ተዛውረው ታስረው ይገኛሉ።
በፖሊስ መምሪያው ምንም ዓይነት ምግብ የማይቀርብላቸው ሲሆን በራሳቸው ገንዘብ በፖሊሶች መልካም ትብብር እየገዙላቸው ህይወታቸውን እስካሁን አቆይተዋል። እጅግም ተጎሳቁለዋል።
አሁን በአካልን ነፃ ማውጣት ህግ ከእስር እንዲለቀቁ ሁላችንም የምንችለውን በማድረግ ልንረዳቸው ይገባል።
የደረሰባቸውን እንግልት ወደፊት ከእራሳቸው አንደበት እንሰማዋለን።
በለጠ ጌትነት

Leave a Reply

Your email address will not be published.

231844348 975072589730765 3360721185381364699 n
Previous Story

አሁን ጦርነቱ ያለው ትግራይ ውስጥ አይደለም: አማራ ምድር እና አፋር ምድር ነው! – ባየ ተሻገር

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
Next Story

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

Go toTop