የፊታችን አርብ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በሚኒሶታ የተቃውሞ ሰልፍ ያደርጋሉ

March 20, 2013

(ዘ-ሐበሻ) በሚኒሶታ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የፊታችን አርብ ማርች 22 ቀን 2013 በስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት በሃይማኖት ተቋማት ላይ በግልጽ በመግባት እያደረገ ያለውን ህገ-ወጥ ተግባር ለማውገዝ የተቃውሞ ሰልፍ አዘጋጁ።
በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ባዘጋጁት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊና ኢትዮጵያን ወዳጅ እንዲገኝ ጥሪ ያቀረቡት አስተባባሪዎች ሰልፉ አራት ዐላማዎች እንዳሉት ለዘ-ሐበሻ አስረድተዋል።
1ኛ. በስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ጣልቃ በመግባት እያደረገ ያለውን ህገ-ወጥ ተግባር ለማውገዝ
2ኛ. መንግሥት በሕዝባችን ላይ እያደረሰ ያለውን የማስፈራራት እና የማሰር ብሎም የመግደል ተግባራት ለመቃወም
3ኛ. የመንግስት ታጣቂ ኃይሎች በቅርቡ በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ ያደረሱትን ግድያና እስራት ለማውገዝና
4ኛ. አወሊያን ማዕከል አድርጎ የተቋቋመውንና እየተንቀሳቀሰ ያለውን የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ድጋፋችንን ለመግለጽ የሚሉ ናቸው።
በሚኒሶታ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ሠልፍ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል። የተቃውሞ ሰልፉ የሚደረግበትን አድራሻ የያዘውን ፍላየር ይመልከቱ።
ይህ በ እንዲህ እንዳለ በሚኒሶታ የሚገኙ የ ክርስትና እምነት ተከታዮች ከሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጎን በመቆም በዚህ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በመገኘት ” በስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ጣልቃ በመግባት እያደረገ ያለውን ህገ-ወጥ ተግባር ለማውገዝ” በጋራ እንደሚሰለፉ ድጋፋቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።

Previous Story

የተቃዋሚዎች ድክመትና ለስልጣኑ ያላቸው ርቀት (ተመስገን ደሳለኝ)

Next Story

ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን በኪራይ ሰብሳቢነትና በፀረ ዲሞክራሲያዊነት ፈረጀ

Go toTop