ጥር 2 ቀን 2012 ዓም በአዲስ አበባ ሆቴል ዲአፍሪክ በተካሄደ የመጽሃፍት ባዛር ላይ በታሪክና በፖለቲካ የከፍተኛ ትምህርትና የእምነት ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ሃገራዊ ሃላፊነት በአግባቡ ይወጡ ዘንድ ማሳሰቢያ ተሰጠ::
“ኢትዮጲያ 2012 መጽሃፍት ምረቃና ባዛር” ላይ የተገኙ “በሀገራችን ካሉት በጣት ከሚቆጠሩት የዩንቨርስቲ ሴት መመህራን አንዷ “የኬሚስቶች እናት” የሚባሉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ ዶ/ር ድርሻዬ መንበሩ በዪኒቨርስቲ እንስት ምሁራን ትኩረት እንደማይሰጣቸው ቅሬታቸውን ገለጹ:: በዚሁ ስብሰባ ላይ ሌላው ተናጋሪ ቄስ ማርቆስ ሃደሮ በሃገራችን የሃይማኖት ሰዎች የሚፈራረቁት መሪዎችን እየተቀበሉ ማስተጋባት ወይም መሸሽ እንጂ ለምድራዊና ሰማያዊ ሃላፊነት ያለመትጋታቸውን ገለጹ:: ለሃገራችን ተገቢው ፍትህ መስፈን ቤተሃይማኖቶች ትልቅ ድርሻ ስላላቸው ዘመኑን በመዋጀት የሚጠበቅባቸውን ሃገራዊ ሃላፊነት በቅንነት ይወጡ ዘንድ ቄስ ማርቆስ መክረዋል::
ሁለቱም ተናጋሪዎች ምሁራንና የእምነት ሰዎች ለበጎ ለውጥ ምሳሌ መሆን እንደሚኖርባቸው በአጽንኦት ሲገልጹ ዶክተር ድርሻዬ ለዘመናት ባገለገሉበት የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በዚህ መሰሉ መድረክ ላይ የመናገር እድል ቀርቶ ተገቢ ትኩረት እንደተነፈጋቸው ቅሬታቸውን ለታዳሚዎቹ አሰምተዋል::
ፕሮግራሙ የተከናወነው በአሜሪካ የኢትዮጲያ ኮሚኒቲ አስተባባሪ አደፍርስ (ኤዲ) ሃብቴ መካሻ ሁለት መጽሃፍት ምረቃና የመጽሃፍት ባዛር በተደረገበት ወቅት ሲሆን በስፖንሰርነት ይደግፉ ዘንድ ከተጠየቁት መሃል የምስራች ድምጽ መገናኛ ዘዴዎች ብቻ ዴሬክተሩ አቶ ገመችስ ዲዲ የመጽሃፍትን ጠቃሚነትና የእውቅት ምንጭነት በመዘርዘር ተናግረዋል:: በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ የደራሲው ወላጅ እናትና የማይጨው አርበኛ የወ/ሮ ልኬለለሽ በያን ባልደረባ የወሮ ጥሩነሽ ወልደአረጋይ ልጅ ወ/ሮ ተረፈች አስፋው ልጃቸውን ለተባበሩ ደራሲያንና የሚዲያ ሰዎች ምስጋና አቅርበዋል::
ሚዛናዊ ታሪክና ፖለቲካ የአደንዛዥ እጽና የአልኮል መጠጥ ሱስ ምክሮች ሁለት መጽሃት በይፋ በተመረቁበት ፕሮግራም ከገበያ ውጭ የሆኑ ጠቃሚ መጽሀፍትን የሚሰበስቡ አቶ ብርሃኑ ጥርሳምብ ብርቅዬ መጽሃፍቶቻቸውን በማቅረብ የመጽሃፍት ፍቅራቸውንና የዘመናት የአንባቢነት ታሪካቸውን ለታዳሚዎቹ አውግተዋል::
ይህን መሰሉ የንባብብ ባህል አሳዳጊ ፕሮግራም በሌሎችም ዘንድ በተለይ በዳያስፖራው ኮሚኒቲ ዘንድ እንዲጎለብት ተሳታፊዎቹ አበክረው ጠይቀዋል::
በወቅታዊ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ልዩ ልዩ ጽሁፎቹን የሚያቀርበው ደራሲው አደፍርስ (ኤዲ) ቃልምልልሶች ከዚህ ቀደም በኢሳትና በአውስትራሊያ የአማርኛ ሬዲዮ ፕሮግራሞችና በኦማሃ ሄራልድና በከተማው ቻነል ስድስት ቴሌቪዥን ቀርቧል::
የዜና ምንጭ- የኢትዮጲያ ኮሚኒቲ ኦማሃ ነብራስካ