በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አሳሳቢ ሆኗል | ከግማሽ በላይ የመንግሥት ሠራተኞች ትክክለኛ የትምህርት ማስረጃ የላቸውም

March 20, 2017

ከሙሉቀን ተስፋው

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ የጤና ተቋማትና ትምህርት ቤቶች ላይ የሚሠሩ አብዛኛዎቹ ትክክለኛ የትምህርት ማስረጃ እንደሌላቸው መረጃዎች አመለከቱ፡፡ ሀሰተኛ የትምህርት ዝግጅት ማስረጃ በማቅረብ የሚቀጠሩት አብዛኛዎቹ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች እንደሆነም የመረጃ ምንጫችን ገልጧል፡፡

አብዛኛዎቹ የመምህራን እና የጤና ባለሙያዎች ቅጥር እንደ ነቀምትና ሻሸመኔ ባሉ የኦሮሚያ አካባቢዎች እንደሚፈጸም የጠቆሙት ምንጮቻችን በፎርጅድ የተሠሩ የትምህርት ማስረጃዎች ለቅጥር ይቀርባሉ ተብሏል፡፡

ጉዳዩ ያሳሰበው የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ 60 የሚሆኑ ከነቀምትና ከአሰላ የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች ተመርቀና ብለው ያስገቡትን መረጃ እንዲመረመር ለትምህርት ተቋማቱ ቢላክም ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ የትምህርት ማስረጃቸው ሊገኝ አልቻለም ተብሏል፡፡
የዐማራ ተወላጆች ኦሮምኛ አይችሉም እየተባሉ በዞኑ እንደማይቀጠሩ የገለጹት ምንጮች ቀደም ሲል በመምህርትነት የመጡ አሁን የዞኑን የካቢኔ በመቆጣጠር ለማንኛውም ቅጥር በኦሮሚያ አካባቢ እንደሚከናወን ነው የተነገረው፡፡

Previous Story

ዶ/ር መራራ ጉዲና እና እስክንድር ችሎት ላይ ተናገሩ | ”ህዝባዊ እንቢተኝነት በየትኛውም ሀገር እንደ ሽብር ተቆጥሮ አያውቅም”

Next Story

በሳንጃ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ በተወረወረ ቦምብ 6 ሰዎች ቆሰሉ | ከፋኝ ጦር አስተዳዳሪው ቤት ላይ የቦምብ ጥቃት አደረሰ

Go toTop