
አሊ ሞሐመድ ይሱፍ ላለፉት ሥምንት ዓመታት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር የነበሩት ሙሳ ፋኪ ማኅማትን ይተካሉ። ይሱፍ የተመረጡት የኬንያው ጉምቱ ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ እና የማዳጋስካር የቀድሞ የኤኮኖሚ እና የፋይናንስ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶን አሸንፈው ነው።
የአፍሪካ ኅብረት 38ኛ ዓመታዊ የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ ሲጀመር የአንጎላው ፕሬዝደንት ዮዋዎ ሎሬንሶ የዓመቱን የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበርነት ከሞሪታኒያው ፕሬዝደንት ሞሐመድ ዑልድ ተረክበዋል።
የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ቀውስ እና የሱዳን ጦርነት በጉባኤው ትልቅ ትኩረት ከሚሰጣቸው ርዕሰ ጉዳዮች መካከል እንደሚሆኑ ይጠበቃል። አሜሪካ የምትሰጠው ሰብአዊ ርዳታ መቋረጥም የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ዓመታዊ ጉባኤን ትኩረት የሚስብ ነው።
DW