“ስንትና ስንት የሚጻፍበት ሞልቶ በሞተር ብሽክሊትና በአማራ መጻፍ ምን የሚሉት ቀልድ ነው” የሚለኝ እንዳይኖር አደራ፡፡ በታዬኝ አቅጣጫ የታየኝን እጽፋለሁ፡፡ በርዕሴ የጠቀስኳቸው ሁለቱ እጅግ በሚያሣዝን ሁኔታ እየተሰቃዩ ስለታዘብኩ ነው ቢያንስ ሰው እንዲያዝንላቸው ይህን የምጽፈው፡፡
የመሥሪያ ቤታችን ሞተረኛ በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከሚሠራበት ጊዜ የማይሠራበት ጊዜ ይበልጣል፡፡ ምክንያቱን ስንጠይቀው በዚህ ዘመን በአዲስ አበባ ሞተር ሣይክል የሚነዳ እንደዘራፊና ወንጀለኛ ስለሚቆጠር በጣም እየተሰቃዩ እንደሆነ ነገረን፡፡ ያኔ ነው ይህ ርዕስ ብልጭ ያለብኝ፡፡
ልጁ እንደነገረኝና ከሌሎችም ጠይቄ እንደተረዳሁት በአሁኑ ወቅት ይህ ከፈሱና ከገዛ ጥላው ሳይቀር የተጣላ የ666 አጋፋሪ ሰውዬ አዲስ አበባን በቁጥጥሩ አስገብቶ አዲስ አበቤን ፍዳውን እያበላ ነው፡፡ ሌላው ሁሉ ቀርቶ እንቅልፍ እምቢ ሲለው በደረቅ ሌሊት እየተነሣ ከተማዋን በመዞር የተኙ ሰዎችን ይቀሰቅስና “መጋረጃችሁን በዚህና በዚህ ቀለምና ዲዛይን ቀይቀሩት፤ አሁን ያለው ለዚህ አካባቢ አይመጥንም፡፡ የግድግዳችሁን ቀለምም ግራጫ አድርጉ፡፡ የመብራት አምፖሉም ይቀየር፡፡…” እያለ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ የወሰዳቸውን ንጹሓን ዜጎች እየቀሰቀሰ እንደሚያስጨንቅ ይነገራል፡፡ እነዚህኞቹ እንዲያውም ከአማራዎቹ ሲነጻጸሩ ዕድለኞች ናቸው፡፡ ይታይህ እንግዲህ – 130 ሚሊዮን ሕዝብ አንዱን ከአንዱ በማጋደልና ሀብት ንብረታቸውን በመቀማት ሣይሆን በፍትኅና ርትዕ እንዲያስተዳድር የሚጠበቅበት ሰውዬ የወረዳ ወርዶ ታች ድረስ ዘቅጦ የግለሰቦችን ቤት መብራትና ውኃ፣ የቤት ቀለምና የመጋጃ ዲዛይን ሲቆጣጠርና ቀስ ብሎም – መቼም ይሄም አይቀርም – አለባበሳቸውን እንዲቀይሩ ሲያስገድድ፡፡ ወይ መዓልቲ አለ ሐጎስ! እናንተው ትሻሉኝ ነበር፡፡ ወያኔን የሚያስናፍቅ ዕብድ ይግጠመኝ?
አማራ ግን በዚህ የኦሮሙማ መንግሥት የማያየው አበሳና ፍዳ የለም፡፡ ከአዲስ አበባ ለመፈናቀል፣ ቤትን በዶዘር ለማፈራረስ፣ እሥር ቤት ገብቶ ለመበስበስ፣ በነፃ እርምጃ ለመገደል፣ በርሀብ ተጠብሶ ለመሞት… በምክንያትነት አማራነት ከበቂ በላይ ነው፡፡ በፀጥታ ኃይሎች መታወቂያህ ሲፈተሸ ሦስቱም ስሞችህ የአማራ ከሆኑ የሚጠብቅህ ፍዳ ሲዖል ሳትሄድ እዚሁ ሲዖል የገባህ ያህል ነው፡፡ አማራ መሆንና በአቢይ ጥቁር መዝገብ ውስጥ መገኘት ጅሃነምን ለሚያስመርጥ ረመጥ የመጋለጥ ያህል ነው፡፡
እንደውነቱ ሞተር ሣይክል በየትኛውም ዓለም በጣም የሚፈለግና የሚመከርም የመጓጓዣ ዓይነት ነው፡፡ በሩቅ ምሥራቅ ሀገራት ባለሥልጣናትና ሀብታሞችም ይጠቀሙበታል፡፡ የሚያኮራ እንጂ የሚያሣፍርም ነገር የለውም፡፡ የኔዘርላንድስ ጠ/ሚኒስትር ይጠቀም የነበረው ብስክሌት ነበር – ሞተር ብስክሌት ሳይሆን ተራ ብስክሌት፡፡ ጤነኛ ሰው በሚያስተዳድሯቸው ሀገራት ሁለት እግራ ተሸከርካሪዎች ከነዳጅ ፍጆታ፣ ከጊዜ ቁጠባ፣ ከአካባቢ ብክለትና ከኢኮኖሚ ቁጠባ አኳያ በጣም ስለሚፈለጉ እንደኦህዲድ በፈለጉ ጊዜ የሚታገዱ ሣይሆኑ ዜጎች እንዲጠቀሙባቸው የሚመከር ሀገራዊ ረብ ያላቸው ናቸው፡፡
እዚህ ኢትዮጵያ ግን ያው ሁሉም ዓለም አቀፍ ህግጋትና ደምቦች ወደኢትዮጵያ ሲገቡ ድምበራችንን ከመሻገራቸው እዚያው አየር ላይ ስለሚበለሻሹ ሀገራችን የደነዞች መናኸሪያ ከሆነች ሰነባበተች፡፡ አሁንማ ጨርሶ ለይቶላታል፡፡ ስንትና ስንት ታላላቅ ሰዎች – የህክምና ዶክተሮች – ኢንጂነሮች – መምህራን – ፊዚዮቴራፒስቶች – ወጌሻዎች – ነርሶች – ልጅና ዐዋቂ በየቤቱ አስጠኚዎች – ሣይኮሎጂስቶች – ሳይኪያትሪስቶች – ስንቱን ብዬህ – እነዚህን የመሰሉ ማኅበራዊ አገልግሎት ሰጪዎች ሁሉ በሀገራችን በሞተር እየተንቀሳቀሱ የዕለት እንጀራቸውን ያገኛሉ፤ በአገልግሎታቸውም የሥጋና የመንፈስ በረከታቸውን ለሚፈልጉ ሁሉ ያድላሉ፡፡ እነዚህ ደነዞች ግን በአንዲት አፈ ቀላጤ “ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እስከዚህ ድረስ ሞተር ሣይክል እንዳይነዳ” ይሉልህና ይህን ሁሉ ዜጋ ቤቱ ያውሉታል፡፡ ጭካኔ ነው፤ ድድብናም ነው፡፡ ዜጎች ላይ ሞት እንደማወጅ ነው፡፡ በዚያ ላይ አገር ምድሩን የያዘው አዲሱ ቤተ መንግሥት በአንድ ያበደ ሰው ትዕዛዝ በዚያ አካባቢ በአሥር ኪሎ ሜትር ሬዲየስ ውስጥ ሞተር ዝር እንዳይል ተደርጓል፡፡ የምትገርም ሀገር እየሆነች ነው፡፡ የሰሞኑ የሞተር እገዳማ ምድረ … (ስድቡን ተውኩት) አላንዳች አህጉራዊ ጥቅም ለሴትና ለቅንጦት ለሚመጡ እርባናቢስ መሪዎች ሲባል መሆኑ በእጅጉ ያበሳጫል፡፡ ከንቱ ስብሰባ፡፡ አንድም ፍሬ የሌለው ለ“ተሰበሰቡ” ብቻ የሚደረግ ገንዘብ ፈጅ ስብሰባ፡፡ ያቺ የባርባዶስ ጠ/ሚኒስትር ግን ልጅ ይውጣላት – ልጅ ካላት፡፡ አቀመሰቺው አሉ – በነገር፡፡
በመሠረቱ ወንጀልን መከላከል መጥፎ አይደለም፡፡ ነገር ግን ወንጀልን በመከላከል ሰበብ የዜጎችን የመኖር መብት በዚህን ያህል ደረጃ መገደብና ለረሀብና ለችግር መዳረግ ትልቅ ዕብሪት ነው፡፡ እርግጥ ነው – አሁን እንደዚህ ያለውን ዕብሪት የሚቀጣ ምድራዊ ኃይል ላይኖር ይችላል፡፡ ነገር ግን የዕንባን አጸፋ የሚችለው እንደሌለ ማንም ሊረዳ ይገባል፡፡ የሕዝብን ገንዘብና ሀብት እየዘረፉ በትሪሊዮኖች የሚገመት ብር አልባሌ ማፍሰስ አሁን እዩኝ እዩኝ እንዳስባለ ሁሉ ነገ ደግሞ ደብቁኝ ደብቁኝ የሚያስብልበት አጋጣሚ ይከሰታል፡፡ እናም ይህ ሰውዬ ጥጋብና ዕብሪቱን መቀነስ እንዲችል ወዳጆቹ እነዳንኤል ክብረት ቢመክሩት ጥቅሙ ለነሱም ጭምር ነው፡፡ በነገራችን ላይ ወንጀልን መከላከል የሚያስችሉ ብዙ ዘመናዊና ነባር ቴክኒኮች እያሉ ቀላሉን አማራጭ መጠቀም “ሰሊጥ ውስጥ ያለሽ መጭ አብረሽ ተወቀጭ” እንደማለት ነው፡፡
ለማንኛውም አዲስ አበባ ለአማራና ለሞተር ሲዖል ሆናለች፡፡ የሚደርስላቸውም ያለ አይመስልም፡፡ ከተማዋ ውስጥ አንድም አማራ እንዳይገኝ የሚደረገው ሁለገብ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን በየመሥሪያ ቤቱ ስትሄድ በሚያጋጥሙህ ምንም ዓይነት የሥራ ችሎታ የሌላቸው ሠራተኞች፣ የቋንቋ ችሎታም ብቻ ሣይሆን የሃሳብ ማመንጨት ድርቀትም አጠናግሮ በደፋቸው አዳዲስ የኦሮሙማ ሠራተኞች ተሞልቶ ስታይ በድንጋጤ የምትገባትን እያጣህ የሀገርህን ለይቶላት መውደም ትረዳለህ፡፡ “ፀጉራም ውሻ አለ ሲሉት ይሞታል” እንዲሉ ሆኖ ግን ኢትዮጵያ የሚለው ስም በሚዲያዎች ሲጠራ ስንሰማ በርግጥም ኢትዮጵያ ያልሞተች የሚመስለን ብዙ ነን፡፡ አማራውም ከተዞረበት አፍዝ አደንግዝ አልነቃ ብሎ ተቸገርን፡፡ ነገን የሚያስበው አማራ ጥቂት ሆነና በማዎቅም ይሁን ባለማወቅ ወይም “እኔን ከተመቸኝ ለማን ጀቴ ብዬ” ከሚል ራስ ወዳድነት ብዙዎቻችን ትናንትንና ዛሬን ወደነገ ለማዞር የምንባዝን ሆንን፡፡
ማይሙ ካሊጉላ አቢይ አህመድ እንዳሻው የሚፈነጭባትና ያሻውን ነገድ በየተራ የሚያጭድባት ኢትዮጵያ ተፈጥራ ሣለ ይህን አንደርባዊ ጉድ ላለማየት እንደሰጎኗ ጭንቅላታችንን ወደመሬት የምንቀብር ዜጎች በዝተናል፡፡ ይሁንና አይደርስብንም ያልነው በሌሎች ላይ የደረሰ መዓት በየቤታችን ገብቶ እያንጫጫን ይገኛል፤ እንዲህም ሆኖ ግን “ተው እንዳታስጨርሰን፤ የኔን እግር እየቆረጠመ ነው” እንዳለው ቦቅቧቃ ሰውዬ ሆነን ተራችንን የምንጠብቅ ጥቂት አይደለንም፡፡ መረገም ከዚህ በላይ የለም፡፡
በዚህ መሀል ነው እንግዲህ “15 ሚሊዮን ዶላር ኢትዮጵያ ለሱዳን ረዳች” የሚል ቀልድ በሰሞኑ ከካሊጉላ አንደበት የሰማነው፡፡ “የራሷ አርሮባት የሰው ታማስል” ይላል ያገሬ ባላገር፡፡ እነዚህ ሰዎች ግን ከቁጥርም ከምድርም ከሰማይም ከሁሉም ጋር እንደተጣሉ ዕድሜያቸውን ሊጨርሱ መሰለኝ፡፡ እውን ኢትዮጵያ 15 ሚሊዮን ዶላር እንኳን ለሱዳን ለአዘርባይጃን ልትረዳ ትችላለች? – ማለቴ እንኳን ለጎረቤት ጠላት ለሩቅ ባይተዋር ለማለት ነው፡፡ ይሄ ልጅ ግን በዚህ ደረጃ ያበደው እነዚያ የኢሉሚናቲ ሥውር ማኅበር አለቆቹ ምን ቢያቀምሱት ይሆን? የኔ ነገር … ስለአማራና ሣይክል ተነስቼ ሳበቃ… በሉ በሰላም ያገናኘን፡፡ ኢትዮጵያም የአማራን ደም ጠጥቶ ከማይረካው፣ የአማራን ሥጋ በልቶ ከማይጠግበው፣ በአማራ ስቃይ ጮቤ ከሚረግጠው ከዚህ ጉግማንጉግ ዕብድ ማሙሽ ነፃ ለመሆን ያብቃት፡፡
አሜን!!
–