“ጉድና ጅራት በስተኋላ ነው” እንደሚባለው፣ 99%ቱን የፋኖ ሰራዊት እያስተዳደሩ እንደሆነ አይናቸውን በጨው አጥበው የተናገሩት የውሸት አባቶች መጨረሻ ላይ ጉዳቸው ፈልቷል።
የዳውንቱ ድርድር ዋና አላማ በእስክንድር ስር የተጠረነፉ ጥቂት ፋኖዎችን ለጠላት አሳልፎ ማስረከብ ብቻ አልነበረም፣ ይልቁንም ከእስክንድር ውጭ ባሉት ፋኖዎች ስም ጭምር ተደራድሮ ሲያበቁ ድርድሩን የማይቀበሉትን በአሸባሪነት ካስፈረጁ በኋላ ከጠላት ጋር ተባብረው መውጋት ነበር። አይናቸውን በጨው አጥበው 99%ቱ የፋኖ ሀይል በኛ ስር ነው እስከማለት የደፈሩትም ይህንኑ አላማቸውን ለማሳካት እንደሚረዳቸው ተማምነው ነበር።
የ99%ቱ ቀደዳ ግን ሊወጡት የማይችሉበት ቅርቃር ውስጥ ከቷቸዋል።
በምስጢር የፈፀሙት የክህደት ድርድር የተጋለጠባቸው ጥቂት የእስክንድር ነጋ ተቀላቢዎች፣ በደርድርና ውይይት መካከል ስላለው አንድነትና ልዩነት በስራቸው ለሚገኘው ሰራዊት ለማስረዳት ሞክረው ነበር አሉ። ሰራዊቱን ማሳመን ግን በየሚድያው ላይ እየዞሩ ዘመነ ካሴን እንደመሳደብ ቀላል አልሆነላቸውም ተብሏል። ይህውም ያልጠበቁትና ሊመልሱት የማይችሉት ጥያቄ ከሰራዊቱ መቅረቡ እንደሆነ ለመረዳት ችያለሁ።
በስራቸው ለሚገኝው ፋኖ ስለድርድርና ውይይት አንድነትና ልዩነት ለማስረዳት በሞከሩበት ቦታ ሁሉ የገጠማቸው የመጀመሪያው ጥያቄም፡ “በድርድርና ውይይት መካከል ስላለው አንድነትና ልዩነት ለእኛ ከማስረዳታችሁ በፊት፣ እኛ የማናውቀው ነገር ግን እናንተ ብቻ የምታውቁት 99%ቱ የእስክንድር ፋኖ የት እንደሚገኝ ልትነግሩን ትችላላችሁ? የሚል ነበር አሉ። ሁለተኛው ጥያቄ ደግሞ: “እኛስ ስለምታወሩት ነገር ከናንተ በላይ እናውቃለን፣ ባናውቅ እንኳን፣ መሬት ላይ የምናውቀውን እውነታ ገልብጣችሁ 99%ቱ የአማራ ፋኖ በናንተ ስር እንደሆነ በሚድያ ላይ ለማውራት ያላፈራችሁ ደፋሮች፣ ስለማናውቀው ድርድርና ውይይት አስረድታችሁ ልታሳምኑን የምትሞክሩት፣ እንዴት ብትንቁን ነው? የሚል ነበር አሉ። ቀጥሎም “ለመሆኑ እኛ ብንቀበላችሁስ፣ ከዚህ በኋላ የናንተን ወሬ የሚያምን ህዝብ ይኖራል ብላችሁ ታምናላችሁ ወይ”? የሚል ጥያቄም ቀርቧል ተብሏል።
በዚህ ተስፋ የቆረጡት ተላላኪዎችም ውይይቱን አቋርጠው ሌላ የእስክንድር ታማኝ ሰው በእስክንድር ቦታ ከተኩና ሰራዊቱ እንዳይበተንባቸው ካረጋጉ በኋላ ነገ በሚመሰረተው የአማራ ፋኖ አንድነት ውስጥ የሚፈልጉትን የአመራርነት ቦታ መያዝን የመጨረሻ አማራጭ ማድረጋቸው ተሰምቷል።
ሰራዊቱ ግን ከዚህ “በኋላ እየሱስ ክርስቶስን እንኳን በአካል ብታመጡት ልናምናችሁ ስለማንችል፣ አትድከሙ” ብሎ እንቅጩን ነግሯቸዋል።
የእስክንድር ተላላኪዎችም የ99%ቱ ፕሮፓጋንዳችን ጉድ አደረገን በማለት ፀጉራቸው እየነጩ ነው አሉ።
እኛ በበኩላችን በካፈርኩ አይመልሰኝ እልህ ከድጡ ወደ ማጡ ከምትገቡ ይልቅ እስክንድር የሚባልን አሳሳች ዲያቢሎስ አስወግዱና ንሰሀ ገብታችሁ ወደ ወንድሞቻችሁ ትቀላቀሉ ዘንድ እንመክራለን።