ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደሮችን ሾመ

November 6, 2018

የለውጥ እርምጃ እየሰራሁ ነው ያለው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው እለት ለአምስት አምባሳደሮች ሹመት ሰጥቷል፡፡ ሹመት የተሰጣቸው አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ፣ አምባሳደር ማህሌት ኃይሉ፣ አምባሳደር ዶ/ር ቦጋለ ቶሎሳ፣ አምባሳደር ነጋ ፀጋዬ እና አምባሳደር ደዋኖ ከድር መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ገልጻል፡፡ በሹመቱ መሰረትም፡-
አምባሳደር ወይንሽት ታደሰ የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ጉዳዮች ቋሚ ተጠሪ
አምባሰዳር ማህሌት ኃይሉ የአውሮፓ፣ የአሜሪካ፣ የኤዥያ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ቋሚ ተጠሪ፣
አምባሳደር በጋለ ቶሎሳ የዳያስፖራ እና ቆንስላ ጎዳዮች ቋሚ ተጠሪ
አምባሳደር ነጋ ፀጋዬ የኃብት ማኔጅመንትና አገልግሎት ቋሚ ተጠሪ
አምባሳደር ደዋኖ ከድር ደግሞ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ቋሚ ተጠሪ ሆነዋል፡፡
አምባሳደር ወይንሸት በሲዊዲን አምባሳደር እንዲሁም በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ የነበሩ ሲሆን አምባሳደር ማህሌት ኃይሉ ደግሞ በኒውዮርክ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቋሚ መልዕክተኛ ጽ/ቤት ምክትል የሚስዮን መሪ በመሆን ያገለገሉ ናቸው፡፡ አምባሳደር ዶ/ር ቦጋለ ቶሎሳና አምባሳደር ደዋኖ ከድር ደግሞ በኩባ አምባሳደር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን አምባሳደር ነጋ ፀጋዬ አምባሳደርና የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጄነራል በመሆንም ሰርተዋል፡፡

በኩዌት ኢትዮጵያዊትየቤት ሰራተኛዋን የገደለችው ሴት መከሰሷን ገልፍ ኒውስ ዛሬ ዘግቧል፡፡ ጋዜጣው በዘገባው ድርጊቱ የተፈፀመው አል ፌርዳውስ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ውስጥ መሆኑን ገልፆ፣ ተጠርጣሪዋ ዛሬ ፍርድ ቤት እንደቀረበችና ምርመራው እክሲጠናቀቅ ለ21 ቀናት እስር ቤት እንድትቆይ እንደተወሰነ አስረድቷል፡፡ የኩዌት አቃቤ ህግ በተጠርጣሪዋ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ ግድያና ህገ ወጥ ሰው የማዘዋወር ክስ እንደመሰረተባትም ዘግቧል፡፡ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው ተጠርጣሪዋ በኢትዮጵያዊን በዱላ ደብድባ እንደገደለቻት ማስረጃዎች አሉ ብሏል፡፡ የተጠርጣሪዋ ጠበቃ ግን ደንበኛው ሆን ብላ ለመግደል አስባ ሳይሆን የቤት ሰራተኛዋን ለመቅጣት ብላ ባደረገችው ድርጊት ሁኑታው መፈጠሩን ገልፀው መከራከራቸውን ጋዜጣው አስረድቷል፡፡ የቤት ሰራተኛዋን ከደበደበቻት በኋላ ወደህክምና ቦታ ያልወሰደቻት ፖሊስንና እስርን በመፍራት እንደነበር ተጠርጣሪዋ ተናግራለች እንደዘገባው፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=0OBDIk-J-Do&t=71s

Previous Story

በጎንደር እጃቸው የያዙት ቦምብ ይሰራል አይሰራም በሚል ሲከራከሩ ፈንድቶ አራት ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ

Next Story

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አርብ አማራ ክልል ናቸው

Go toTop