የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አርብ አማራ ክልል ናቸው

November 7, 2018

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ዓርብ ጎንደር ከተማ የሚገቡ ሲሆን፥ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል ያደርጉላቸዋል። በቆይታቸውም በጎንደር እና አካባቢው የሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎችን እና የልማት ስራዎችን እንደሚጎበኙ፥ የጎንደር ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ሞገስ ተናግረዋል።
የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት በሃገር ደረጃ የተጀመረውን ግንኙነት እንደሚያጠናክረው ታምኖበታል።
በጎንደር ከተማ በርካታ ኤርትራውያን በተለያየ ስራ ተሰማርተው ይገኛሉ።
ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ የተመራ የልዑካን ቡድን በአስመራ ጉብኝት ማድረጉ የሚታወስ ነው።
—-
https://www.youtube.com/watch?v=LCftg3owFj4&t=4s

Previous Story

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደሮችን ሾመ

Next Story

አብን ቢሮ የተጠለሉት የወልቃይት ተፈናቃዮች በፖሊስ ተከበናል ሲሉ ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረቡ፣ ፖሊስ በበኩሉ ‹‹የከበባኳቸው ለደህንነታቸው ነው›› አለ

Go toTop