በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የዓለም ሕዝብ የሥልጣኔ ቁንጮ ላይ በደረሰበትና ሁሉም የዐለም ሕዝብ በሙያውና በዕውቀቱ በጥበቡና በብልሀቱ እንዲሁም በመተባበሩና በአንድነቱ ሀገሩን በማልማትና በማበልፀግ በሀገሩ ውስጥ ከብሮና በልጽጎ እንዲሁም ተከብሮ በሚኖርበት በዚህ ዘመን የአማራ ሕዝብ (ነገድ) አማራ ባልሆንኩ ይሻለኝ ነበር (ወይ አማራ መሆን!) ይሻለኝ ነበር እያለ በስቃይና በመከራ ባህር እያወኘ ይገኛል።
እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ ውስጥ ከመቶ 50 ፐርሰንት የሚሆነውን የሕዝብ ብዛት የያዘው የአማራ ሕዝብ መሆኑ ግልፅ ነው። ይህም የአማራ ሕዝብ ሀገሩንና ወገኑን እምነቱንና ባህሉን ወጉንና ልማዱን ወዳድ በመሆኑ ከሌላው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረ ሰቦች ጋር በፍቅርና በሰላም አንድ በሆን አጥንቱን ከስክሶና ደሙን አፍስሶ ፊትአውራሪ በመሆን ሀገሩ ኢትዮጵያን እዚህ ያደረሳት የተከበረው ይህ ታላቅ የአማራ ሕዝብ ነው። ነገር ግን አሁን ይህ አምባገነን እና ሰው በላ ጨፍጫፊ የሆነ ዐቢይ አሕመድ እና የእሱ የዘራፊና የሽፍታ ስብስብ ቡድን የፍቅር መፍለቂያ በሆነው በአማራው ሕዝብ እገዛ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ ወርቅ ላበደረ ጠጠር እንዲሉ በባለውለታው በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት እና በአጠቃላይ ከሀገሩ ከኢትዮጵያ የማፅዳት እርምጃ እየተወሰደበት እና እየሞተ እንዲሁም እየተሰደደ ይገኛል።
በዚህም ምክንያት አረመኔው ዐቢይና ግብርአበሮቹ በዚህ በተከበረ የአማራ ሕዝብ ላይ ይህን አይነት አረመኔያዊ ድርጊት ሲፈጽሙበት እንዲሁም እናቶች እና በአጠቃላይ ልጅ አገረዶች በአደባባይ ሲደፈሩ ጨቅላ ሕፃናቶች ሲታረዱና ሲገደሉ አዛውንት ሽማግሌዎች የታመሙ ሕመምተኞች ከተኙበት አልጋ ላይ መሬት ለመሬት እየተጎተቱ በስቃይ ሲሸኙ የሚወልዱ እናቶች በምጥ ላይ እያለ በጭንቅ ሲገደሉ ሆስፒታል ለመታከም የገቡ በተኙበት በድሮን ሲቃጠኑ ለትምህርት ክላስ ውስጥ የተሰበሰቡ ህፃናትን በመድፍና በላውንቸር ከአፈር ጋር ሲደባልቋቸ አማራ ባልሆንኩ ይሻለኝ ነበር እስከማለት ደረሱ።
ይህም የአማራ ሕዝብ ይህንን አይነቱን ግፍና በደል መቋቋም ቢያቅተውና ወደ ዓለም መንግሥታትም ቢጮህ ሰሚ በማጣቱ እራሱን አደራጅቶና ጫካ ገብቶ እየተፋለመ መሞትን መረጠ።
ይህም አረኔው ዓቢይና ግብረ አበሮቹ ይህ አይነት የሙፈፅሙት ግፍና በደል አልበቃ ብሏቸው አማራው ስንገድለው ለምን ዝም ብሎ አይሞትም በሚመስል መልኩ በአዲስ አበባና በሁሉም ክልል የሚኖሩ የአማራ ተወልጅ የሆኑትን በመለየት ቤታቸውን በማፍረስ ንብረታቸውን እና ገንዘባቸውን በመውረስ ሲያሰቃዩአቸው አማራ ባልሆንኩ ይሻለኝ ነበር አሉ።
ለምን ያለ አግባብ ቤታችን ይፈርሳል ሀብት ንብረታችንስ ለምን ይወረስብናል ብለው ጥያቄ ስላቀረቡ ብቻ በወህኒ የተወረወሩና ተገድለውና አስከሬናቸው በአስፋልት ላይ ተጥሎ ብሎም በጫካ ውስጥ አስከሬናቸው በአውሬ ተበልቶ የሚገኙ ስፍር ቁጥር የላቸውም።
ይህንንን አረመኔያዊ ድርጊት እያዩ ከፍራቻ የተነሳ ዝም በማለት ከመናገር ቢቆጠቡም እንኳን ከሰለባው ማምለጥ አልቻሉም 20 እና 30 ሚሊዮን ብር አምጡ በመለት በመልእክተኛ ሲጠየቁ በድንጋጤ ከቆሙበት ተፍገምግመው በመውደቅ እየሞቱ ያሉ ብዙዎች ናቸው።
በአጋጣሚ ይህንን ገንዘብ ተጠይቀው ሳይከፍሉ እና በህይወት እንኳን የተርፉ ቢኖሩ ድንገት መጥተው አፍነው ወስደው ሲያሰቃዩ ቆይተው ገድለው ጥለዋቸው የሚገኙ ብዙዎች በመሆናቸው በዚህ ዘመን አማራ ባልሆንኩ ይላሉ።
በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ አማራ የሆነ ሁሉ ማንነቱ እየተጠና ከአያት ከቅድመ አያት ጀምሮ ርስት ጉልቱ እና ይዞታው የሆነ ቦታውን እየተነጠቀ ያለግምት ቤቱን እያፈረሱ እና እያፈናቀሉ በመልሶ ማልማት ሰበብ ለኦሮሞ ባለሀብት በመስጠት ኦሮሞን ለማበልጸግ አማራውን ለማደኸየትና ብሎም ለማጥፋት በተነደፈ እስትራቴጂ እነሱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የኦሮሞ ባለሀብት ግንባታውን ካጠናቀቀም በኋላ በቀላል ዋጋ ቅድሚያ ለኦሮሞ ሕብረተሰብ እየታደለ ይገኛል።
በመቀጠል በውድ ዋጋ በውጭ ለሚኖረው ዲያስፎራ እየሸጡ አሁንም የኦሮሞ ባለሥልጣናት የአማራውን ብሎም የኢትዮጵያንን ሀብትና ንብረት በመቀራመት ሀብትን በማካበት በተለያዩ የውጪ ሀገራት የመኖሪያ ቤትና ድርጅትን እየከፈቱ ይገኛሉ።
ይህ አልበቃ ብሏቸው ከእነሱ ግድያና ጭፍጨፋ አምልጦ ወደ ውጭ በስደት የወጡትን የአማራ ተወላጆች በሆኑ ዜጎች ላይ ሰላም በማሳጣት በስደት ጥያቈያቸው መሠረት ካስጠጓቸው የውጭ ሀገራት ጋር በመነጋገር የስደት ጥያቄያቸው ተቀባይነት እንዳያገኝ በማድረግና ወደ ሀገራቸው ኢንዲመለሱ በማድረግ በእነሱ ስም ከሚመልሷቸው ሀገራት መንግሥታት ገንዘብ ፈንድና የተለያዩ የርዳታ ቁሳቁስ እየተቀበሉባቸው በአሁኑ ሰአት ብዙ የአማራ ተወላጆችን ከስደት ወደ ሀገር ቤት በማስመለስ እያሰቃዩአቸው ይገኛሉ።
አሁንም በስደት በውጭ ያሉ የአማራ ተወላጆች ጥያቄያቸው ተቀባይበት ያላገኘና መልስ በመጠባበቅ ያሉ ሁሉ ይህንኑ ድርጊት በመፍራት በጥገኝነት ከነበሩበት ሀገር ወደሌላ ሀገር ሲሸሹና ሲያመልጡ በሚደርስባቸው አደጋ እየሞቱ ያሉ የአማራ ተወላጆች ብዙዎች በሆናቸው አማራ ባልሆን ይሻለኝ ነበር በማለት የአማራው ሕዝብ በዚህ አይነት መከራና ስቃይ ይገኛል።
ስለዚህ ያለው አማራጭ ጭቁኑን የአማራን ሕዝብ ነጻ ለማውጣት እና ሀገራችን ኢትዮጵያን ብሎም መላው የኢትዮጵያን ሕዝብ ከዚህ አረመኔና ገዳይ ጨፍጫፊ የሽፍታ ጥርቅም ቡድን ነጻ ለማውጣት የሚታገለውን ፋኖን እንደግፍ።
የነጻነት አምላክ እዚአብሔር ኢትይጵያን ነጻ ያውጣልን።
ወይ አማራ መሆን