
ባለፈው ሳምንት ሃሙስ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ “አንገሽ” ቀበሌ ተፈፀመ በተባለ የድሮን ጥቃት 16 ሠዎች ሲገደሉ 10 ያክል መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። ጥቃቱ የተፈፀመው በሱቆችና ሻይ ቤቶች በነበሩ ንፁሐን ዜጎች ላይ እንደሆነ ነዋሪዎቹ ገልፀዋል። የአካባቢው የመንግሥት አስተዳደር ደግሞ ጥቃቱ የፋኖ ታጣቂዎች እንደመጠለያ በሚገለገሉበት ትምህርት ቤት ላይ መሆኑነና ሟቾቹም ታጣቂዎች ናቸው ሲሉ ተናግረዋል። ከአንድ ዓመት በላይ የሆነዉ እና እስካሁንም መሻሻል ያልታየበት የአማራ ክልል የሠላም እጦት አሁንም ለነዋሪዎቹ እንግልት፣ ጉስቁልና፣ ስቃይና ስጋት ሆኖ እንደቀጠለ ነው። ጦርነቱን ተከትሎ በርካታ የድሮን ጥቃቶች ተፈፅመዋል፣ በርካቶችም ህይወታቸው አልፏል፤ የአካል ጉዳትም የደረሰባቸው ብዙዎች ናቸው። በምሽቱ ስርጭታችን ዘገባ ይዘናል፤ ተከታተሉን!
DW Amharic