መፀለይ አሁን ነው ! – አሸናፊ ዋቅቶላ፣ ሕ/ዶ -የውስጥ ሕክምና ባለሙያ 

March 18, 2023
ቋንቋው በረከተ ፣ መግባቢያው ቀነሰ፣
አንባጓሮ በዛ፣ ማዳመጥ አነሰ፣
ወጣት ጯሂ ሆነ፣ ባዛውንቱም ባሰ፣
አማኝ ነኝ የሚለው፣ እዚያም ያልደረሰ፣
ሁሉም ዓለም ይላል፣ዓለም ዓለም ዓለም!
ከራሱ በስተቀር፣የሚያስብ  ግን የለም።
           ~ዘመኑ ጨለመ ፣ ተስፋ መነመነ፣
           መፀለይ አሁን ነው፣ ያመነ ያላመነ!
መነጋገር ቢኖር፣ ባለከፋ ነበረ፣
በመጯጯህ ብዛት፣ ሁሉም ደነቆረ፣
ያጓራል ለብቻው ፣ ያጓራል በጋራ፣
ቁልቁል እየሮጠ፣ ትውልድ ሆኖ ተራ፣
ያራዳ ጎርምሳ ቤተ-እምነት ዘለቀ፣
ቀዳሽ አስቀዳሹም፣ ማዋከብ አወቀ፣
          ~ ዘመኑ ጨለመ ፣ ተስፋ መነመነ፣
           መፀለይ አሁን ነው፣ ያመነ ያላመነ!
ሕዝብን ሜዳ ጥሎ፣ ብር እያሳደደ፣
ተው ባዩ ጠፋና፣ ባንድላይ  አበደ፣
ወርቅ ሰላም ሞልቶ፣ በሁሉ ሰው ቤት፣
የብር ግርግር፣ ከተተው አዘቅት፣
ሞላጫው ዘራፊ፣ ምኑንም ሳያውቅ፣
ፈላስፋ ሆነብን፣በጊዜ  መድርቅ።
          ~ ዘመኑ ጨለመ ፣ ተስፋ መነመነ፣
           መፀለይ አሁን ነው፣ ያመነ ያላመነ!
አሸናፊ ዋቅቶላ፣ ሕ/ዶ -የውስጥ ሕክምና ባለሙያ
ሲልቨርስፕሪንግ ሜሪላንድ- ዩ ኤስ ኤ
ማርች 18፣ 2023

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ በህወሓት ተመረጡ

Next Story

ከግርማ የሺጥላ ጋር የተሰዳደቡት ባለስልጣን ተባረሩ | በደሴ ተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ

Go toTop