በወለጋ ውስጥ እንዲሁም በጉጂና በሰሜን ኦሮሚያ አማራ አዋሳኝ አከባቢዎች ሰራዊቱን አሰማርቶ ከመንግስት ሃይሎች ጋር ውጊያ የገጠመው ይህ ታጣቂ ቡድን በተለያዩ ጊዚያት ያሰለጠናቸውን ታጣቂዎቹን በማሰማራት ከፍተኛ የሆነ ውድመት እና ግድያ እየፈፀመ መሆኑ ይታወቃል።
ያሰለጠናቸውን ታጣቂዎቹን በስፋት ጦርነት ባለባቸው የከሚሴና አጣዬ እከባቢዎች እንዲሁም በወለጋ እንደሚያሰማራ ከድርጅቱ ኮሚኒኬ የተነበበ መረጃ ይጠቁማል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰሜን ኦሮሚያ በኦነግ ታጣቂ ሃይሎች እና በመንግስት የትሰጥታ ሃይሎች መካከል ከባድ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑ ታውቁል፡
የደረሰን ቪዲዮ እንደሚያሳየው በሰሜን ኦሮሚያ አማራ አዋሳኝ አከባቢዎች ላይ በከባድ መሳሪያ የተደገፈ ጦርነት አየተካሄደ ነው ፡ የኦንግ ሰራዊት እባላት በተለያዩ ወረዳዎችና የመንግስትን ንብረት በማውደም እና ሰዎችን በመግደል ላይ መሆናቸው ተነግሩአል።
መረጃ