የአማራ ብልጽግናዎች የተገፉበትና የተሸማቀቁበት የብልጽግና ስብሰባ – ግርማ ካሳ

February 28, 2022

የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ማድረጉ፣ ስብሰባው በሰላም መጠናቀቁ መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡ አቅጣጫዎችን አስቀምጠናል ማለታቸው፡፡

ምን ተነጋገሩ፣ ምን አይነት አቅጣጫ አስቀመጡ፣ እነ ማን ነበሩ በስብሰባው ? …..የሚታወቅ ነገር አልነበረም፡፡

በቀጣዩ የድርጅቱ የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተደረገ፡፡ ስብሰባው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ ተባለ፡፡ አሁንም ምን እንደተነጋገሩ፣ ማን እንደነበረ ወዘተ ይፋ አልተደረገም፡፡ በገደግዳሜው አቅጣጫዎች አስቀመጥን የሚል አጭር መግለጫ አወጡ፡፡

ከተለያዩ ማእዘናት ትችት ሲበዛባቸው፣ ከአመራሩ የተወሰኑቱ እርስ በርስ የሚጋጭ፣ ምን አይነት የሚረባ ይዘት የሌለው፣ ውሸት የበዛባቸው አስተያየቶች ሰጡ፡፡ እነ ሙፈሪያት ከሚልና አቶ ብናልፍ አንዷለም ያሉ፡፡ በጥቅሉ የብልጽግና ፓርቲ ምን እያደረገ፣ ምን እየሰራ እንደሆነ፣ ምን እንዳቀደ፣ ቨጨለማ ከሕዝብ ደብቆ ውሳኔዎች እያሳለፈ ነው፡፡

የሜዲያ አንዱ ስራ እውነትን ፈልቅቆ ማውጣት እንደመሆኑ፣ ኢትዮ360 የተደበቀውን በማውጣት በማእከላዊ ኮሚቴ የነበረውን ሁኔታ ለህዝብ ይፋ አድርጓል፡፡ በሰብባው ስለነበሩ ዝርዝር ሁኔታዎች በስፋት ወደፊት እመለስበት ይሆናል፡፡ ግን ለዛሬ ኢትዮ360ን ሃቢ በማድረግ ጥቂት ነጥቦችን ላስቀምጥ፡

1ኛ የብልጽግና ፓርቲ 100% ከብልጽግና ፓርቲነት ወደ በዳዲና ወይም ኦህዴድነት እየተቀየረ መሆኑን፣

2ኛ አንጋፋ የአማራ ክልል አመራሮች፣ አቶ ገዱ አንዳራጋቸውንም ጨምሮ፣ የብልጽግና ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባን ቦይኮት እንዳደረጉ፣

3ኛ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራርና ጨምሮ ሶስት አመራሮች መሰረታዊ የሕዝብ ጥያቄዎችን አቅርበው፣ ክብርን በሚነካ መልኩ በጠቅላዩ መዘለፋቸውን፣

4ኛ የአዲስ አበባን ስም በይፋ ወደ “ፊንፊኔ – አዲስ አበባ” ለመቀየር መወሰኑን፣

5ኛ በጦርነቱ ዙሪያ ፣ ከጦርነቱ ጋር በተገናነ በሕዝብ ላይ ያለውን አደጋ ወዘተ ምንም አይነት ውሳኔ አለመወሰኑን፣

ነው መረዳት የተቻለው፡፡

በተለይም ኢትዮ360 ስለ አቶ ደመቀ መኮንንና አቶ ብናልፍ አንዷለም ያቀረበው አስቂኝ ከመሆኑ ባሻገር ፣ ስዎቹ ምን ያህል ስልጣናቸውን ላለማጣት የሚበረከረኩ፣ በጭራሽ ልግል ጥቅማቸው እንጂ ለሕዝብ ጥቅም ያልቆሙ መሆናቸው ለማሳየት የሞከረው፡፡ እኔ ለነርሱ አፈርኩ፡፡ እንደያዙት ስልጣን ትልቅነት፣ ተጽኖ መፍጠር ሲችሉ፣ በዚህ መልኩ የተልከሰከሱ መሆናቸው ያሳዝናል፡፡ ለሁለት ቀን አንዲት ቃል ሳይተነፍሱ፣ የነርሱን ስልጣን የሚመለከት ሲሆን ነው ለመነጋር የተነሱት፡፡በተለይም አቶ ደመቀ መኮንን፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ሆኖ እንዴት ዶ/ር አብይ አህመድ ለሰዓታት ሲናገር ፣ እርሱ ለአንድ ሁለት ደቂቃ ብቻ፣ አንድ ጊዜ ይናገራል ? እንዴት ዶክተር አብይ አህመድ እየደጋገመ በተከይም የአማራውን ማህበረሰብ ክብር ሲደፍር ዝም ብሎ ይመለከታል ? ይህ ሰው የአማራ ብልጽግና መሪ ነኝ ባይ ሆኖ በዚህ መልኩ ራሱን ማዋረዱ፣ በሌላ አባባል የአማራ ማህበረሰብን ነው ያዋረደው፡፡

ስለሰሊጥ ሌባዎችም ተነስቶ ነበር፡፡ አቶ አብርሃምና አቶ ተሻገር ሌባ ተባልን ብለው ነው መሰለኝ አስተያየት ለመስጠት እጆቻቸውን ቢያነሱ ዶር አብይ ኢግኖር ነው ያደረጋቸው፡፡ እነርሱም ቢሆኑ በዚህ መልክ ሲዋረዱ ፣ ልክ ሕጻን ልጅ በባርጩሜ ሾጥ ሲደረግ ዝም እንደሚለው፣ ዝም ማለታቸው አስገራሚ ነው፡፡ እኔ እነርሱን ብሆን እድል አልሰጥ ሲለኝ ስብሰባዎች ረግጬ እወጣ ነበር፡፡

ለማንኛው የብልጽግና ነገር ራሱን በራሱ እያፈረሰ ያለ ድርጅት ወደ መሆን እየመጣ ነው፡፡ እንደነ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ አቶ ዮሐንስ ቧያሌው ያሉ አንጋፋ የአዴፓ ሰዎች እየሸሹት ያለ ድርጅት በአማራ ክልል ውስጥ በአማራ ማህበረሰብ ዘንድ ቀጣይነት አይኖረውም፡፡ የአቶ ዥንጥራርም ጠንካራ አቋም በአዲስ አበባ ውስጥ የኦህዴድ ኃይል ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ እንደማይሆንለብት አመላካች ነው፡፡

በነገራችን ላይ ማረጋገጥ አልቻልኩም እንጂ፣ ምን አልባት ጻዲቅ አብርሃና ዶር አብርሃ በላይ ሊገኙ ቢችሉም፣ አብዛኞቹ የትግራይ ብልጽግናዎች በዚህ ስብሰባ ይገኛሉ ብዬ አላስብም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የዘንድሮው 126ኛው የዓድዋ በዓል በእኔ ሚንስትርነት ዘመን በዳግማዊ ዓፄ ምንሊክ አደባባይ አይከበርም

Next Story

አድዋ!!!

Go toTop