የወቅቱ ባህልና ስፖርት ሚንስትና የአንዱ ኦነግ ክንፍ ሊቀመንበር የሆኑት ኦቦ ቀጀላ መርዳሳ የዘንድሮው 126ኛው የዓድዋ በዓል በእኔ ሚንስትርነት ዘመን በዳግማዊ ዓፄ ምንሊክ አደባባይ አይከበርም በሚለው አቋማቸው በመፅናታቸው በዓሉ እስከ ዛሬ ይከበርበት ከነበረው የምንሊክ አደባባይ ወደ አድዋ ድልድይ እንዲዛወር ተደርጓል። የኦቦ ቀጀላን ውሳኔ በመቃወም አንጋፋው የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ቅሬታውን ቢያቀርብም ኦቦ ቀጀላ አሻፈረኝ ብለዋል። በዚህም መሠረት ለዓድዋ በዓል የተዘጋጀው ኤግዚቢሽን ከብሔራዊ ሙዚዬም ወደ አብርሆት ቤተመጻሕፍት፣ የበዓሉ ማክበሪያ ከምንሊክ አደባባይ ወደ ዓድዋ ድልድይ እንዲቀየር ተደርጓል።
ኦቦ ቀጀላ የፖለቲካ ፓርቲወን አይዲዎሎጂ እናከብራለን። ሀገርን ወክሎ መስራትና ፓርቲን ወክሎ መስራት የተለያዩ በመሆናቸው በቀሩት ሁለት ቀናት ወደ ሀገራዊ አስተሳሰባቸው ተመልሰው በዓሉ በተለመደው በምንሊክ አደባባይ ይከበር ዘንድ የግል አመለካከታቸውን ገተው ሕዝባዊ አመለካከለት ይላበሱ ዘንድ እንመክራለን
ፔጥሮስ አሸናፊ