አ ባ ይ የአገር አባት የአገር ሲሳይ መሆኑ ተመሰከረ። እልልልልልልልልል..! መኮንን  ሻውል ወልደጊዮርጊስ

February 20, 2022

  እንኮን ደስ አለን። የአገር ልጆች። ፈጣሪ የለገሰን ትልቁ ወንዛችን አባይ የአባት ወጉን  በዜጎች ፍቅር የሞላበት ትብብር ና ርብርብብ  ዛሬ የካቲት 13/2014 ቀን አሳየን። እንሆ!  መጋቢት 24/2003  የተጀመረው፣ ታላቁ የህዳሴ የኃይል ማመንጫ ግድብ ሥራ ብሥራት ከ 11 ዓመት በኋላ፤ ዛሬ፣ በሁላችንም ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን  አሥተዋፆ  ኃይል ማመንጨት ጀመሯል።  የካቲት 13/2013 ዓ/ም። እልልልልልልልልልልልልልልልልልል…!

ዓባይ ማለት የናይል ወንዝ ታላቁ ገባር ወንዝ ሲሆን መነሻው ኢትዮጵያ ነው። አባይ 70 በመቶ የሚሆነው የሀገሪቱን ወንዞች የውሃ ድርሽ ሲይዝ አጠቃላይ የውሃ ድ ርሻውም ቢሆን 50 በመቶ የሚጠጋ ነው። በኢትዮጵያ ከዓባይ ውጭ ያሉት ወንዞች ድምር ድርሻ 30 በመቶ ነው።

ስለዚህ አባይ ለግብጽና ሱዳን ዋና የውሃ ና የብልፅግናቸው  ምንጭ እንደሆነው ሁሉ፤ ለኢትዮጵያም፣ ዓባይ ወሳኝ የህልውናዋ ቀጣይነት ማረጋገጫ፣ አባት ወንዟ መሆኑን  የታችኛዎቹ ተፋሰስ አገሮች በውል መገንዘብ  ያለባቸው ቀን ዛሬ ነው።

ኢትዮጵያ የአባይን ውሃ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ የመጠቀም መብት አላት ። ለታችኞቹ ተፋሰስ  አገራት በተገቢው መልኩ ውሃችን  እንዲደርስም  ምንጊዜም ተባባሪ ና ለጋሥ  መሆኖን ደጋግማ ገልፃለች ።    ኢትዮጵያ ሌሎቹን የአባይ ተፋሰስ ሃገሮች በማይጎዳ መልክ በአግባቡ የተቀየሰውን “ታላቁ የሕዳሴ ግድብ”  ገንብታ  700 ሜጋ ዋት አመንጭታ “ እንሆ በረከት ! “ ለዜጎቿ  ማለቷ  ፤ በግብፅም ሆነ በሱዳን ህዝብ ላይ ግድቡ የሚያስከትለው ጉዳት እንደሌለ በተጨባጭ ያሳየ በመሆኑ በኢትዮጵያውያን ለጋሥነት ማንም ሊጠራጠር  እንዳይችል አድርጓል   ። ( የእድገትና የብልፅግና ፀሮች ግን ዛሬም ይኽ ኃቅ እንደማይዋጥላቸው ይታወቃል ።)

ደስታዬን የተሟላ ለማድረግ ፅሑፊን በዚህ  ግጥም እቋጫለሁ ።

አባይ !

አባይ !  አንተ አ ባ ይ !
ዛሬ ሆንክ ፣ የአገር አባት
የሀገር ፣ የወገን  ሲሳይ  !

ድህነትን ተዋጊ
አገርን አበልፃጊ
ሌሎችንም ጠቃሚ
ቅን እና በጎነትን ዓላሚ ።

ዓባይ ! አንተ አ ባ ይ
የኢትዮጵያዊያን ሲሳይ !

እንሆ ዛሬ አሣየኸን
“እንሆ  በረከት ! “ አልከን
በብርሃን  አጥለቀለቅኸን
የብልፅግና ተስፋን አመለከትከን ።
እልልልልልልልልልልልል…!
አ ባ ዬ ! ዛሬ  አሳኘኸን ።

አ ባ ይ ! ውድነህ  አ ባ ይ !
የአገር የወገን የዘላለም ሲሳይ  !
ልጆችህ ጋር ድህነትን ታግሎ ጣይ !
አ ባ ይ ! አ ባ ይ ! …

2013 ዓ/ም

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ኢትዮጵያዊነት፣ HR6600ና ወቅታዊ ጉዳዮች – የመፍትሄ ሃሳቦች- ከአባዊርቱ

Next Story

በእብደት ላይ እብደት እየጨመሩ ያሉት የአድዋ ልሂቆች – ነጋሪት

Go toTop