“ጦርነትን በእነ ቢቢሲና ሲኤንኤን የፈጠራ ወሬ ማሸነፍ አይቻልም” ኬንያዊው ፖለቲከኛ

November 4, 2021
ጦርነቱን በእነ ሲኤንኤን፣ ቢቢሲና ሌሎች የምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃን የፈጠራ ወሬ እናሸንፋለን ብለው ተስፋ የሰነቁ ካሉ አሸባሪው ሕወሓት ድል ያደርጋል ብለው ዘላለም ሲጠብቁ ይኑሩ ሲሉ ኬንያዊው ፖለቲከኛ ፋራህ ማሊም ገለፁ።
የኬንያ ብሔራዊ ጉባኤ የቀድሞው ምክትል አፈ ጉባኤ እና የፓርላማ አባል ፋራህ ማሊም ሙሃመድ የሽብር ቡድኑ ሕወሓት ንፁሃንን እያጠቃ ወደ አጎራባች ክልሎች በገባ ቁጥር እየተከበበና ተጠርጎ የሚወገድበትን ሁኔታ እየፈጠረ ነው ብለዋል።
አዲስ አበባ እገባለሁ ብሎ የፎከረውና ከመደበቂያ ዋሻው የራቀው የሽብር ቡድኑ በፈፀመው ስህተት ራሱን እያጠፋ እንደሆነም ጠቁመዋል።
ኬንያዊው ፖለቲከኛ “ኢትዮጵያ አፍሪካዊ ናዚ የሆነውን አሸባሪውን ሕወሓት የግድ ማስወገድ አለባት፤ ይህን የማድረግ አቅሙም አላት” ሲሉ ከሰሞኑ መግለፃቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው።
ዋልታ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

በጓሃ ጽዮን ወረዳ ተፈናቅለው ሜዳ ላይ ያሉ ወገኖቻችን አስቸኳይ ድጋፍ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ተናገሩ

Next Story

የፋኖው ቅሬታ – ወራሪው የትግሬ ሃይል በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት

Go toTop