በጓሃ ጽዮን ወረዳ ተፈናቅለው ሜዳ ላይ ያሉ ወገኖቻችን አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ተናገሩ።
አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ
በጓህ ጽዮን ወረዳ በአንድ ቀን በሰዓታት ብቻ 500 ቤት በማቃጠል ከ5 ሽህ በላይ አማራዎች መፈናቀላቸውን የገለጹት በአዲስ አበባ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች መንግስት ንጹሃንን እንዲታደግ አሳስበዋል።
ከቢስቲኖ ጤና ቀበሌ ልዩ ስሙ ሙግደጤራ አካባቢ ተፈናቅለው በተለይም በደራ እና በጓሃ ጽዮን ከተማ ያለመጠለያ ሜዳ ላይ የሚገኙ ወገኖች አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ነው ያሉት።
ከመንግስት በተጨማሪም የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና የሚዲያ አካላት እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብም ሊደርስላቸው ይገባል ብለዋል።
ከአሚማ ጋር ቆይታ ያደረጉት ወጣት ታደሰ እና ወጣት ቢኒያም መንግስት መዋቅሩን ባለመፈተሹ ወገኖቻችን ለከፋ ችግር ተዳርገዋል ነው ያሉት።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአካባቢው ያሉ አማራዎች በቋንቋቸው እንዲዳኙ እንዲሁም በቂ የትጥቅ እና የስልጠና ድጋፍ እንዲያገኙ ከመስራት ይልቅ በክልከላ እና በዝምታ እየተባበረ ነው ሲሉም ወቅሰዋል።
ወጣቶቹ ከአሚማ ጋር ያደረጉትን ቆይታ በዩቱብ አድራሻችን የምናቀርብ ይሆናል።