በኢትዮጵያዊያን እየተመከተ ያለው የአሸባሪው ሕወሓት ወረራ

October 31, 2021

tplf

ዓለም ዐቀፍ ሕግጋትን በጣሰው የሕዝባዊ ማዕበል የጦርነት ስልት ወረራና ጥቃት የከፈተው አሸባሪው ሕወሓት እየተመከተ ነው።

የሽብር ቡድኑ ያለ የሌለ ኃይሉን አሰባስቦ በሕዝብ ማዕበል ወደ ጦርነት የገባው ንብረት ለመዝረፍና ያልቻለውን ለማውደም፣ የወደመበትን የጦር መሳሪያ መተኪያ ፍለጋ እና በሕዝብ ማዕበል መንግሥት ላይ ጫና በማሳደር ወደ ድርድር ለማምጣት በሚል ከንቱ ምኞት ነው።
ለዚህም አጠቃሁ ሲል ድምፃቸውን የሚያጠፉ፤ የወገን ጦር ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተሻግሮ መጠነ ሰፊ እርምጃ ሲወስድበት በሰብኣዊ ድጋፍ አቅርቦት አጀንዳና የተደራደሩ ጥያቄ ሽፋን የሚጮኹለትን መንግሥታት፣ ዓለም ዐቀፍ ድርጅቶችና መገናኛ ብዙኃንን ከኢትዮጵያ በዘረፈው ገንዘብም ጭምር ቀጥሮ የጥፋት አጀንዳውን ቀጥሏል።
ሆኖም የሽብር ቡድኑ እየተደመሰሰ የወገን ጦርም ይዞታውን እያሰፋ መሆኑን ለዋልታ የደረሱት መረጃዎች ይጠቁማሉ።
መንግሥት እድሜ እና አካላዊ ብቃቱ የፈቀደለት ዜጋ ሁሉ የክተት ጥሪውን ተቀብሎ ወራሪውን የሽብር ኃይል ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋትና የአገሩን አንድነት ለማስጠበቅ እንዲዘምት ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል። በዚህም ሕዝቡ ለጥሪው በጎ ምላሽ እየሰጠና ለዘመቻ እየተነሳ ይገኛል።
ኢትዮጵያዊያን በአንድነት እንዲነሱና ጠላታቸውን እንዲቀብሩ የክልል መንግሥታት ጥሪዎችን እያቀረቡ፤ ጦርነቱም የአንድ አካባቢ አለመሆኑንና ዘርፈ ብዙነቱን እያስገነዘቡ ይገኛል።
በግንባር አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ከሰርጎ ገቦች በንቃት እንዲጠብቁ፤ ለአገር መከላከያ ሰራዊትና አብረውት ለተሰለፉ የፀጥታ ኃይሎች ደጀንነታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ ቀርቧል።
ጥቅምት 21/2014 (ዋልታ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የመግለጫ ጋጋታ ከጥቃት አያድንም፤ #ነፃነት በነፃ የለም፤ ከንግሥት ይርጋ (ጎንደር)

Next Story

የአገር መከላከያ ሠራዊት በሁሉም ግንባሮች አሸባሪውን ወራሪ የህወሃት ሃይል በመደምሰስ ላይ እንደሚገኝ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ

Go toTop