ከክልል እስከ ወረዳ ያለ አመራር በአግባቡ ኃላፊነቱን እየተወጣ አይደለም :: ይህን ስል በእጣት የሚቆጠሩ ምሳሌ የሚሆኑትን አመራሮች አይጨምርም ::
በየግንባሩ “እያዋጋን ነው” የሚሉ አመራሮችን አሉበት በተባለው በቦታው እየተንቀሳቀስኩ አይቻለሁ :: በሕዝብ በጀት ሆቴል ተቀምጦ የምግብ እና የመጠጥ በጀት ከመፍጀት ውጪ ግንባር ገብቶ የድርሻውን ወይም ግዴታውን የሚወጣ አመራር የለንም :: አስተያየት ስንሰጥም በጥርስ ውስጥ እንገባለን ::
የሚሠሩ አመራሮችን ምሳሌ አድርገን ስንናገር ጓ-ገጭ የሚለው ብዙ ነው ::
አሻጥር አለ ለሚባለው አሉባልታ እንደ እኔ በመከላከያ ሠራዊታችን ላይ ምንም ዓይነት አሻጥር አለ ብየ አላምንም :: ወታደሩ የሚችለውን ያክል ዋጋ እየከፈለ እየተዋደቀ በዓይኔ እያየሁ ነው ::
ግን ትእዛዙ ከየት እና ለምን እንደሆነ ባናውቅም ፤ በውጊያ ስዓት ላይ “ውጊያውን አቁሙ” የሚል ትዛዝ ይሰጣል :: ወታደር ለምን ? እንዴት ? የሚባል ጥያቄ ማንሳት አይቻልም ምክንያቱም ትእዛዙን የሚሰጡት ፖለቲከኞች ናቸው ::
እንደ እኔ እይታ ሕዝባችን መሪ አልባ ነው:: መንግሥት ምን አለ ? ከማለት እና የመንግሥትን ዲስኩር እና #የመግለጫ ጋጋታ ከመጠበቅ ወጥተን ሁላችንም የምንችል ገብተን በመዋጋት ወይም ስንቅ በማቀበል አለዚያም ቁስለኛ በማንሳት እና በማገዝ ለመከላከያ ሠራዊታችን ለዐማራ ልዩ ኃይል ለፋኖ እና ለምንሻችን የኋላ ደጀን በመሆን ለነፃነታችን እንታገል::
በክልል እና በወረዳ አመራሮች ተስፋ የምታደርግ እርምህን አውጣ :: የእኛ አመራሮች መግዚትነቱን ለምደውታል :: በዚህ ስዓት የህልውና ትግል ከፊታችን ተደቅኖ ሰዎች ስለሥልጣን እከሌ ተሾመ እከሌ ተንሳፈፈ ሲሉ ነው የሚውሉ :: ለሄደ ለመጣው ማሸርገድ ልምዳቸው ነው::
እስካሁን ዋጋ እየከፈለም እየሞተም ያለ መከላከያ ወይም ልዩ ኃይል ፋኖ ምንሻ እንጅ አመራር ከተንደላቀቀ ሆቴል ወጥቶ እንደ ሕውሀት በችግር ጫካ ገብቶ የታገለና ያታገለ የለም ::
ወንድ ሆነው ማታገሉን አያታግሉ ግን የሆነ ከተማ ስጋት ላይ ሲሆን ቀድመው በመፈርጠጥ ሕዝቡን ውዥንብር ውሰጥ ከተው የሚጠፉትን ብታዩ ያሳፍራል:: ነገሩ ሲያልፍ ጠብቀው ተመልሰው አክተር (የድሉ ባለቤት ) ይሆናሉ :: ስለዚህ #ነፃነት በነፃ የለም የመጣውን ጠላት እንደ ሕዝብ መታገል ያስፈልጋል ::
በእየቤታችን ተቀምጠን የግዞትን ቀን አንጠብቅ መብትና ግዴታችን ካወቅን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ወጥተን ግዴታችን እንወጣ ሌላው ሙቶ እኔ ልኑር እሳቤአችን እናስወግድ ::
ድል ዋጋ እየከፈሉ ላሉ ጀግኖቻችን!!!