ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ዋድላ ወረዳ ፣ ኮን ከተማ እንዲሁም በጋሸና አካባቢ የሚገኘውን የአሸባሪ የህወሀት ቡድን በመምታት አኩሪ የጀግንነት ተግባር መፈጸሙን አዛዥ አረጋግጠዋል ፡፡
ጀግኖቹ የሰራዊት አባላት በአካባቢው የሚገኝ የጠላት ፣
የሰውና የመሳሪያ ሀይል በየትኛውም አቅጣጫ እንዳይወጣ በማድረግና በመደምሰስ ከዋድላ ወረዳ እስከ ጋሸና ከተማ በመቆጣጠር ታሪካዊ ድል መፈፀማቸውን አመልክተዋል፡፡
ሠራዊቱ ከወልዲያ አምልጦ የመጣውን ጠላት
በመከታተል ፣ በዋድላ ወረዳና አካባቢ የመሸገውን የጠላት ሀይል እና መሳሪያ በመደምሰስ በከፍተኛ ድል ጋሸና ከተማን መቆጣጠሩን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት የኢዜአ ን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ያድርጉ
ኢዜአ