ፍርድ ቤቱ ፌዴራል ፖሊስ በሽብር ወንጀል የተከሰሱትን እነሌተናል ጀኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳኤን ይዞ እንዲያቀርብ ትእዘዝ ሰጠ

August 20, 2021

tsadikan

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ የፀረ ሽብርና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት በእነሌተናል ጀኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳኤ መዝገብ የተሰከሰሱ ግለሰቦችን ፌዴራል ፖሊስ ከመከላከያ ጋር በመተባበር ይዞ እንዲያቀርባቸው ትእዘዝ ሰጥቷል።

ሌተናል ጀኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳኤ፣ ብርጋዴሬ ጀነራል ምግባረ ኃይሌ እና ብርጋዴር ጄኔራል ታደሰ ወረደን ጨምሮ 74 የጦር መኮንኖች የነበሩ ግለሰቦች ናቸው ክስ የተመሰረተባቸው።
አቃቤ ህግ ሁሉም ተከሳሾች የህወሓት የሽብር ቡድንን ተልእኮ በመቀበል ህገወጥ ወታደራዊ ቡድን በማቋቋም የሰሜን እዝንና የፌዴራል ፖሊስን ብሎም በአማራ እና በአፋር ክልሎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል በሚል በሽብር ወንጀል እንደከሰሳቸው ይታወቃል።
ችሎቱ በግለሰቦቹ ላይ ለዛሬ ክስ ለመመልከት ነበር ቀጠሮ ይዞ የነበረው፤
ይሁን አንጂ ሶስቱ ተከሳሾች ከዳንሻና አዋሽ ማቆያ ሌሎችም ከቃሊቲ ማቆያ በመረጃ ልውውጥ ስህተት ሊቀርቡ አልቻሉም ተብሏል።
በዚሁ መሰረት የፍርድ ቤቱ ትእዛዝ በትክክል ተተግብሮ በአካል የሚቀርቡ 20 ተከሳሾች ለጥቅምት 3 ቀን 2014 ዓ.ም ቀርበው ክስ እንዲነበብ ሲል ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።
በዚሁ ቀን እነ ሌተናል ጀኔራል ፃድቃን ገብረ ትንሳኤ ጨምሮ ያልተያዙ 54 ተከሳሾች በፌዴራል ፖሊና በመከላከያ በትብብር ተይዘው እንዲቀርቡ ሲል ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ አስተላልፏል።
በጥላሁን ካሳ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

236244955 3007732859469173 1442007123964492267 n
Previous Story

በአማራ ክልል ሰርጎ የገባው የአሸባሪው ህወሀት ሀይል መደምሰሱን በሰሜን ወሎ ግንባር የተሰማራው የሰራዊት ክፍል አስታወቀ

Next Story

አሸባሪው ትህነግ/ወያኔ  ከጥቅምት 24/2013  ጀምሮ  የፈፀማቸው ወንጀሎች (በከፊል…) – አለም T

Go toTop