ዛሬ ፍፃሜውን ባገኘው 32ኛው የቶኪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ 4 ሜዳሊያዎችን አግኝታለች

August 8, 2021
232736338 4674513609247145 8418133472080971981 n
232736338 4674513609247145 8418133472080971981 n
ኢትዮጵያ በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ በሜዳሊያ ሰንጠረዥ በአንድ ወርቅ፣ በአንድ ብር እና በሁለት የነሃስ ሜዳሊያዎች (በድምሩ በ4 ሜዳሊያዎች) ከዓለም 56ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 5ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀች።

230325194 4674518545913318 62975039267596519 n

በሰለሞን ባረጋ በወንዶች 10ሺህ ሜትር ፍፃሜ የወርቅ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ሲያስገኝ፤ ለሜቻ ግርማ ደግሞ በ3ሺህ ሜትር መሰናክል የብር ሜዳሊያ ለአገሩ ማስገኘት ችሏል።

229493769 4674518685913304 9091796108545748748 n

ለተሰንበት ግደይ 10ሺህ ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ውድድር የነሃስ ሜዳሊያ ለአገሯ ስታስገኝ፤ ጉዳፍ ፀጋይም በተመሳሳይ በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ውድድር የነሀስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝታለች።

በአሎምፒኩ የመዝግያ ስነ-ስርዓት ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ከፍ አድርጎ የሚያውለበልበው አትሌት ሰለሞን ባረጋ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
በኦሎምፒኩ ኢትዮጵያን በ4 ስፖርቶች የወከሉት 38 ስፖርተኞች ሲሆኑ በአትሌቲክሱ ሶስት አትሌቶች አራተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሮቻቸውን አጠናቀዋል።
በአትሌቲክሱ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ 3ኛ ከዓለም ደግሞ 14ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች።
ከ205 አገራት የተውጣጡ፣ ከ11ሺህ በላይ ስፖርተኞች፣ በ33 አይነት የስፖርት ውድድሮች በተሳተፉበት በ32ኛው ኦሎምፒክ 118 አገራት ምንም ሜዳሊያ አላገኙም።
ኦሎምፒኩ ዛሬ ፍፃሜውን ሲያገኝም አሜሪካ በ113 ሜዳሊያ ከዓለም 1ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ቻይና እና ጃፓን በ88 እና በ58 ሜዳሊያዎች 2ኛ እና 3ኛ ሆነው ያጠናቀቁ ሲሆን ባጠቃላይ 93 አገራት አንድ እና ከአንድ በላይ ሜዳልያ ለማግኘት ችለዋል።
በ2020 የቶክዮ ኦሎምፒክ መዝግያ ስነ-ስርዓት ላይም ከ50 አትሌቶች በላይ የሀገራቸውን ሰንደቅ ከፍ አድርገው ያውለበልባሉ ተብሏል።
EBC

Leave a Reply

Your email address will not be published.

234025259 4230269523760951 2889017138138292904 n
Previous Story

የወልድያ ከተማ ነዋሪዎች የመንግሥትን አፋጣኝ እርምጃ ጠየቁ (ወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን)

229659649 1605320626309592 5975731700981338627 n
Next Story

“አብረን ወደ ፊት እንሄዳለን፤ አብረን የጀግንነት ሥራ እንሠራለን” ኮሎኔል አለበል አማረ

Go toTop