በባሌ ሀገረ ስብከት ሮቤ ከተማና አካባቢው ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር የሚገኘው የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን እስካሁን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ መቃጠሉ ይታወቃል፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=pJpzsue5H3c&t=917s
የተቃጠለውን መልሶ ለመገንባት ዛሬ በተደረገ ገንዘብ ማሰባሰብ ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ማግኘት ተችሏል፡፡ እሳቱን ለማጥፋት የተረባረቡት የእስልምና እምነት ተከታዮች በገንዘብ ማሰባሰቡም ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረጉ ሲሆን የመንግስት ባለስልጣናትም በቦታው በመገኘት ህዝበ ክርስቲያኑን አፅናንተዋል፡፡
–