የወልቃት ጠገዴ አስመላሽ ኮሚቴ ሕዝባዊ ስብሰባ በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ጠርቷል

January 24, 2019

ጥር 19 ቀን 2011 ዓ/ም የወልቃት ጠገዴ አስመላሽ ኮሚቴ ሕዝባዊ ስብሰባ በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ጠርቷል። በውይይቱ ኮሚቴው የሄደባቸውን ርቀቶችና ያጋጠሙትን ፈተናዎች ያቀርባል። ምሁራን ስለወልቃይት ከጥንት እስከ ዛሬ ያለውን እውነታ ያስረዳሉ ተብሏል። ስብሰባውን ለማካሄድ እንዲቻልም የባለሃብቶችን ድጋፍ ኮሚቴው ጠይቋል፡፡ በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ፊርማ የተፃፈው ድጋፍ መጠየቂያ ጥሪ የሚከተለው ነው፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=pJpzsue5H3c&t=917s

ኮሚቴው ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ የህዝብ መድረኮችን በመክፈት ተጨቁኖ የነበረውን ህዝባችን ነፃ ለማውጣት እየሰራ ያለ ኮሚቴ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በአዲ አበባ ከተማ የሚኖሩ የአካባቢው ማህበረሰብ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራምና የውይይት መድረክ ለጥር 19 ቀን 2011 በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ ስላዘጋጀን ውይይቱ የተሳካ እንዲሆን የተለያዩ ወጪዎችን መሸፈን እንዲቻል ድጋፍ ያስፈልጋል፡፡ እርስዎም የበኩልዎን አስተዋፅኦ እንድታደርጉ ትህትናና አክብሮት ጋር እንጠይቃለን፡፡ 

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ አየለ የኮሚቴው ሊቀመንበር

Previous Story

በባሌ ሀገረ ስብከት ሮቤ ከተማና አካባቢው የተቃጠለው ቤተክርስቲያን ጉዳይ…

Next Story

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ለኢትዮጵያ የ130 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ሰጠ

Go toTop